ሴቶች ከወንዶች በላይ በእድሜ ብዙ አመት በመኖር ይታወቃሉ።
ተመራማሪዎች እንደሚሉት ሴት ህፃናት ከወንድ ህፃናት በተሻለ ረሃብ፣ ወረርሽኝ እና ሌሎች ጉዳቶችን የመቋቋም አቅም አላቸው።
ይህም ሴቶች በጨቅላነታቸው ይህ ጠቀሜታ ለማግኘት የሚያስቸሉ ስነ ህይወታዊ የሆነ የባህሪ ልዩነቶች እንዳሉ ተመራማሪዎቹ ጠቁመዋል።
ቨርጂኒያ ዛሩሊ እና ጃምስ ቫውፔል የተባሉት ተመራማሪዎች፥ የምርምር ውጤቶቹ ለፆታዊ ልዩነቱ ሌላ ተጨማሪ ማሳያ ማግኘታቸውን ይናገራሉ።
ተመራማሪዎቹ የ250 ዓመታት በ2 ዓመት እና ከዚያ በታች የአድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያለፉባቸውን አጋጣሚዎች መርምረዋል።
በአሜሪካ እና ትሪናዳድ በባርነት ውስጥ ያለፉ፣ በአየርላንድ፣ ዩክሬን እና ስዊዲን ተከስቶ በነበረው ረሃብ ውቅት የነበሩ እንዲሁም በአየስላንድ በኩሽፍኝ ወረርሽኝ ወቅት የኖሩ ሰዎችን የተመለከቱ መረጃዎችን መርምረዋል።
ጥናቱ እንደሚያመለክተው ሴቶች ከወንዶች ይልቅ በአማካይ ከ6 ወር እስከ አራት ዓመት በሚደርስ ብልጫ ረዥም እድሜ አላቸው።
ውጤቱ በእድሜ ደረጃ ሲታይም ተመራማሪዎቹ እንደሚያመለክቱት የሴት የመዳን እድሎች ብዙዎቹ ገና በሕፃንነታቸው የሚታይ ሲሆን፥ አዲስ የተወለዱ ሴት ህፃናት ከወንዶች ይልቅ ጠንካራ ናቸው ነው የተባለው።
ተመራማሪዎቹ እንደገለጹት ይህ የሴቶች ችግሮችን የመቋቋም አቅም በስነ ባህርይ ወይም ሆርሞን ምክንያት የመጣ ሊሆን ይችላል።
ለዚህም ለምሳሌ የሴቶች ሆርሞን በሽታን ለመከላከል የሚያስችል ጉልበት እንዳለው ታይቶበታል ነው የተባለው።
ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)