በሆድ ጥገኛ ትላትል (ፓራሳይት) መጠቃታችንን የሚጠቁሙ 10 ምልክቶች – 10 Signs You May Have A Parasite

                                                               

1. ከባድ የምግብ ስልቀጣ(መፈጨት) ችግር

የአንጀት ጥገኛ ትላትሎች የአንጀት ሽፋን እንዲያብጥና እንዲጠፋ(እንዲጎዳ) በማድረግ ከባድ ለሆነ ተቅማጥ ይዳርጉናል። በተጨማሪም በጥገኛ ትላትሎቹ የሚመረተው መርዛማ ተረፈምርት ከባድ የሆድ ድርቀት፣ ግሳት፣ የሆድ መነፋት፣ ማቅለሽለሽና የሆድ ማቃጠል ስሜት ያስከትላል።

2. የሆድ ህመም
ሌላኛው በሆድ ጥገኛ ትላትሎች የሚከሰት ችግር የሆድ ህመም ነው። በትንሹ አንጀት ላይኛው አካባቢ የሚገኙ ጥገኛ የሆድ ትላትሎች በዚሁ አካባቢ የእብጠትና ማቃጠል ስሜትን ይፈጥራሉ። ይህም የሆድ መነፋትና የሆድ ህመም እንዲከሰት ያደርጋል።

3. መቀመጫ አካባቢን ማሳከክ
በመቀመጫ አካባቢ ማሳከክ ሌላኛው በሆድ ጥገኛ ትላትል መጠቃት ምልክት ነው።በተለይ በፒን ወርም የተያዙ/የተጠቁ ሰዎች በመቀመጫ አካባቢ ማሳከክና ምቾት ማጣት ይታይባቸዋል። መቀመጫ አካባቢ የሚያሳክክበት ምክንያት ሴቷ ፒንወርም በምሽት ወይም በሌሊት በመቀመጫ አካባቢ ዕንቁላሏን ስለምትጥል ነው።

4. የድካም ስሜት
የድካም ስሜት ምናልባት የሆድ ጥገኛ ትላትል ኢንፌክሽን ምልክት ሊሆን ይችላል።ይህም የሚያያዘው የአንጀት ትላትሎች ከምንመገበው ምግብ ውስጥ የሚገኙ ለሰውነታችን ጠቃሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ስለሚመገቧቸውነው።

5. የምግብ ፍላጎት መቀየርና የሰውነት ክብደት መቀነስ
በምግብ አመጋገብዎ ላይ ድንገተኛ የሆነ ለውጥ ካዮ በተለይ የአመጋገብዎ ሁኔታ ከጨመረ የዚህ ምክንያት ምናልባት በሰውነትዎ ውስጥ ጥገኛ ትላትል ስለሚኖር ሊሆን ይችላል።

6. የአእምሮ ጭንቀት
የሆድ ጥገኛ ትላትሎች የሙድ መቀየር፣ ድብርት እና መብሰክሰክ/መበሳጨት
ሊያስከትሉ ይችላሉ ነገር ግን እነዚህ ምልክቶች ከምግብ ስልቀጣ/መፈጨት ችግር ጋር የተያያዙ መሆን አለበት።

7. ጥርስን ማፋጨት
እንቅልፍ ተኝተው ጥርስዎን የሚያፋጩ ከሆነ አንድ የዚህ ችግር መነሻ ሊሆን የሚችለው የፓራሳይት ኢንፌክሽን ነው። የጥርስ ማፋጨት ዋናው መነሻ መንስኤው በሰውነትዎ ውስጥ የሚገኝው ፓራሳይት የሚለቀው ተረፈ ምርትና መርዛማ ነገሮች ውጤት ነው።

8. የደም ማነስ (በብረት እጥረት)
የአንጀት ራውንድ ወርምና ፒንወርም (roundworm and pinworm) በሰውነታችን ውስጥ የብረት ማዕድን እጥረት እንዲፈጠር በማድረግ ለደም ማነስ ያጋልጡናል።ፓራሳይቱ የብረት ማዕድንን ጨምሮ ሌሎች ጥሩ ቫይታሚኖችን ከተመገብነው ምግብ ውስጥ ይሰርቃል።

9. የቆዳ ችግር
የአንጀት መስመርን የወረሩ ጥገኛ ትላትሎች በሰውነታችን ውስጥ እብጠት በመፍጠርእንዲሁም የተለያዩ የቆዳ ችግሮች ያስከትላሉ ከነዚህ የቆዳ ችግሮች መካከል ሽፍታ ሌሎች የቆዳ አለርጂዎችን ያጠቃልላል።

10. የጡንቻና መገጣጠሚያ ህመም
አንዳንድ ፓራሳይቶች የመገጣጠሚያና ጡንቻዎች ስስ አካሎችን በመውረር ራሳቸውን በሲስት (cyst-like) መሳይ ሽፋን ይከልላሉ። የዚህም ውጤት ማቃጠልና ህመም ያስከትላል። እነዚህ ምልክቶች ከሪህ (Arthritis) በሽታ ጋር በመመሳሰል ብዥታ ይፈጥራል።

ምንጭ:- ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement