የልብ ህመም ከወንዶች ይልቅ በሴቶች ላይ ይከፋል- Heart Disease is Worse for Women Than For Men

                                                         

የልብ ድካም በሽታ ከወንዶች ይልቅ በሴቶች ላይ የከፋ ጉዳት እንዳለው አንድ ጥናት አመለከተ።

ጥናቱ የወንዶች በሽታ ተደርጎ በብዙዎች ዘንድ የሚወሰድ መሆኑን በማንሳት፥ ነገር ግን በልብ ህመም ከተያዙ ወንዶች እና ሴቶች መካከል ሲታይ ሴቶች የበለጠ በበሽታው ለሞት እንደሚዳረጉ አንስቷል።

ተመራማሪዎቹ በ10 ዓመት ጊዜ ውስጥ በልብ ድካም የተጠቁ 180 ሺህ 368 ስውዲናውያን ታካሚዎች ውጤቶችን አጥንተዋል።

የጥናት ውጤቱም በልብ ህመም ከተያዙ ወንዶች ይልቅ ሴቶች የመሞት ዕድላቸው በሶስት እጥፍ ከፍ ያለ መሆኑን አረጋግጠናል ብለዋል።

የብሪታኒያ የልብ ፋውንዴሽን እንዳለው፥ የልብ ድካም ብዙውን ጊዜ የወንዶች የጤና ችግር ነው፤ ነገር ግን ብዙ ሴቶች ከጡት ካንሰር ይልቅ በልብ ሕመም ይሞታሉ።

በሊድስ ዩኒቨርሲቲ እና በስዊድን የካሮሊንስካ ተቋም የሚገኙ ተመራማሪዎች በስዊድን የኦን ላይን የልብ ህመም መዛግብት ላይ ጥናት አድርገዋል።

እንደ ጥናት ውጤቱ በህክምና ምርመራ ወቅት ከወንዶች አንፃር የልብ በሽታ ምርመራ እንዲያደርጉ የሚመከሩ ሴቶች ቁጥር አነስተኛ ሆኖ ተገኝቷል።

ጥናቱን በትብብር ያዘጋጁት የሊድስ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ክሪስ ግሌን፥ ይህ ሊሆን የቻለው በአጠቃላይ የህዝብ ህክምና እና የጤና ባለሞያዎች ላይ የልብ ሕመምተኞች ምን ሊመስሉ እንደሚችሉ በማወቁ ላይ ክፍተት እንዳለባቸው ተረድተዋል።

በጥናቱ እንደተመለከተው በተለምዶ የልብ ድካም በሽታን ስናስብ የስኳር በሽታ ተጠቂ፣ የሚያጨሱ እና ከመጠን በላይ የወፈሩ በመካከለኛ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወንዶችን ነው። 

ይህ ስህተት መሆኑን ያነሳው ጥናቱ ሴቶችም በልብ ድካም በሽታ ይያዛሉ ብሏል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement