ብጉር ምንድነው? – What is Acne?

                                                                                         

ብጉር በሰዉነት ቆዳ ላይ የሚከሰት ችግር ሲሆን የላብ መዉጪያ ቀዳዳዎች( hair follicles) በስብ፣ በሞቱ የቆዳ ሴሎችና አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በባክቴሪያዎች በሚደፈንበት ወቅት የሚመጣ ነዉ፡፡
ብጉር በብዛት የሚከሰተዉ በጣም ብዙ የሆኑ የስብ አመንጪ ዕጢዎች በብዛት የሚገኝባቸዉ የቆዳ ክፍሎች ባሉበት የሰዉነት ክፍሎች እንደ ፊት፣አንገት፣ደረት፣ጀርባና ትከሻ ያሉ ቦታዎች ላይ ነዉ፡፡ ብጉር ከሰዉነት ላይ ሳይጠፋ በሚቆይበትና ከፍ ያለ ደረጃ ላይ ያለ ከሆነ እንደ እፍረትና መንፈስ ጭንቀትን የመሳሰሉ ስነልቦናዊ ጉዳቶችንና የቆዳ ጠባሳን ሊያመጣ ስለሚችል እነዚህ ነገሮች የተጎጂዉን ማህበረዊና የስራ ቦታ ጫናን ሊያመጣ ይችላል፡፡ብጉር ጥሩ የሆነ ህክምና ያለዉ ሲሆን በወቅቱ ከታከመ የሚያመጣዉን የአካልና መንፈስ ጉዳት መቀነስ ይቻላል፡

ለብጉር መከሰት ምክንያቶች ምንድናቸዉ
· የስብ ከመጠን በላይ መመረት
· የሞቱ የቆዳ ሴሎች በአግባቡ ያለመወገድ( Irregular shedding of dead skin cells)
· የባክቴሪያዎች መራባት(መጠራቀም)

ለብጉር ሊያጋልጡ የሚችሉ ነገሮች( Risk factors)
· ለሰዉነት ሆርሞን መለዋወጥ ምክንት የሆኑ ነገሮች በሚኖሩበት ወቅት፡-ጉርምስና፣እርግዝና፣የሴቶች የወር አባበ ዑደት ከመከሰቱ ከ 2 እስከ 5 ቀናት በፊት ያሉ ቀናት፣የተወሰኑ መድሃኖቶችን የሚወስዱ ሰዎች(አንድሮጅን፣ሊትየምና እስቴሮይድ)
· በቆዳ ላይ የሚቀቡ ዘይትነት ወይም ግሪሲ የሆኑ ነገሮች( greasy or oily substances) ወይም የተወሰኑ የመዋቢያ ቅባቶች(ኮስሞቲክሶች)
· በቤተሰብ ዉስጥ የሚከሰት
· በቆዳ ላይ ፍትጊያና ግፊት የሚያሳድሩ ነገሮች፡-ሄልሜንት፣ስልክ፣ጥብቅ ያሉ አልባሳት
ብጉርን የሚያባብሱ ነገሮች(Agravating factors)
· ሆርሞኖች፡-ለምሳሌ በጉርምስና ወቅት አንድሮጂን፣እርግዝና፣ብጉር እያለ የተወሰኑ መድሃኒቶችን መዉሰድ፡-አንድሮጅን፣ሊትየምና እስቴሮይድ
· የተወሰኑ ምግቦች፡-የእንስሳት ተዋፅኦ የሆኑ ምግቦችን እንዲሁም ሃይልሰጪ በብዛት ያላቸዉ ምግቦችን መጠቀም (dairy products and carbohydrate-rich foods)
· ጭንቀት( Stress)
ምንጭ:- ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement