የአንድ ሰው ንጥሻ 100 ሺህ ጀርሞችን በመያዝ 8 ሜትር ይጓዛል – Sneezing

                                                           

ማስነጠስ ሰውነታችን በመተንፈሻ አካል የሚገኙ ቆሻሻዎን የሚያስወግድበት መንገድ ነው። 

ሆኖም ግን በምናስነጥስ ጊዜ በአካባቢያችን የሚገኙ ሰዎችን ልንበክል እንችላለን ይላሉ የጤናው ዘርፍ ተመራማሪዎች።

የአንድ ሰው በሚያስነጥስበት ጊዜ 100 ሺህ ጀርሞች እስከ 8 ሜትር ድረስ በአየር ወስጥ እንደሚረጭ ነው ባለሙያዎች የሚያብራሩት።

ንጥሻው ጀርሞቹን በሰዓት 160 ኪሎ ሜትር የሚጓዝ ተሽከርካሪ በሚኖረው ፍጥነት ጋር እኩል በሆነ ፍጥነት ነው የሚረጨው ተብሏል።

እንዲሁም አንድ ንጥሻ በውስጡ 40 ሺህ ብኛኝ ጠብታዎችን የያዘ መሆኑንም አስታውቀዋል።

ይህም እስከ 100 ሺህ የሚደርሱ ጀርሞች በአፍንጫን በኩል በመውጣት በአካባቢያችን ላይ እስከ 8 ገደማ ድረስ እንዲሰራጩ እንደሚያደርግ የስዊዘርላንዱ ኢዮባስ ኦይል ኩባንያ ተመራማሪ ዶክተር ሮጀር ሀንደርሰን ተናግረዋል።

ምንም እንኳ ንጥሻ ላስነጠሰው ሰው መልካም ቢሆንም በአካባቢው ላሉ ሰዎች ላይ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል ብለዋል ክተር ሮጀር።

በትራንስፖርት ውስጥ በጉንፋን፣ በቲቢና መሰል በትንፋሽ ሊተላለፉ በሚችሉ በሽታዎች የተያዘ ሰው ቢያስነጥስ ከ5 እስከ 10 ደቂቃ ውስጥ የበሽታውን ጀርሞች በማሰራጨት በመኪናው ውስጥ ያሉት በሙሉ በበሽታው ሊበክል እንደሚችል ይናገራሉ።

ይህንን የጤና ችግር ለማስወገድም የህዝብ ትራንስፖርቶች ሁልጊዜም መስኮታቸው ክፍት እንዲሆን ይመክራሉ።

እንዲሁም በሚያንሰጥሰን ጊዜ አፋችንን መያዝ ጀርሞቹ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይዛመት ለማድረግ ይጠቅማል።

ከማስነጠስ ጋር ተያይዘው የሚሱ እውነታዎችን ያብራሉት ዶክተር ሮጀር፥ የማስነጠስ ነፀብራቅ በአብዛኛው የሰውነታችን ክፍል ላይ ይስተዋላል፤ በተለይም ከጡንቻዎቻችን እና ከአይናችን ጋር ግንኙነት አለው ይላሉ።

ለምሳሌም አንድ ሰዎች ሁሌም በሚያስነጥሱበት ጊዜ አይናቸውን የግድ ይጨፍናሉ፤ አይኑን ሳይጨፍን የሚያስነጥስ ሰው የለም የሚለውን ያነሱ ሲሆን፥ በምናስነጥስበት ጊዜ አይናቸውን የማይጨፍኑ ሰዎች ግን ይህ ሊያሳስባቸው አይገባም ብለዋል።

ምንጭ:- ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement