ገላዎን አይታጠቡ የተመገቡት ምግብ በሚገባ እንዲፈጭ የደም ዝውውር ወደ ጨጓራዎ እንዳያዘንብል ያስፈልጋል፡፡ ገላዎን በሚታጠቡበት ጊዜ የደም ዝውውሩ በአመዛኙ ወደ እግር እና እጅ ይሄዳል፡፡ይህም የምግብ መፈጨት ሂደትን ያዛባል፡፡ ምግብ ከተመገቡ በኋላ ቢያንስ ለ30 ደቂቃ መጠበቅ ይኖርብዎታል፡፡  እንቅልፍ አይተኙ ከተመገቡ በኋላ እንቅልፍ ወዲያው መተኛት በጨጓራ ውስጥ ያሉትን ምግብ የሚፈጩ ኤንዛሚዎች ከጨጓራችን ወደ ምግብ ማስገቢያ ጉሮሮ እንዲመጡ ያደርጋል፡፡ ይህም የማቃጠል ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል፡፡  የእግር መንገድ አያድርጉ ምግብን ከተመገቡ በኋላ የእግር መንገድ ማድረግ የምግብ መፍጨት ሂደትን እንደሚያፋጥን የሚታሰብ ቢሆንም በምግብ መፈጨት ጊዜ ለሰውንት ጠቃሚ የሆኑትን ንጥረ ነገሮች እንዳይወስዱ ያደርጋል፡፡  ሻይን አይጠጡ ሻይን መጠጣት የልብ ሕመምን ለመከላከል ጠቃሚነት እንዳለው ቢታወቅም ወዲያውኑ ከምግብ በኋላ መጠጣት አይረንና የተለያዩ ፕሮቲኖች በሰውነታችን እንዳይወሰዱ ያደርጋል፡፡ ፍራፍሬዎችን አይመገቡ፡ ከምግብ በኋላ ወዲያውኑ ፍራፍሬዎችን መመገብ በሚገባ እንዲፈጩ ስለማያደርግ ፍራፍሬዎችን 1 ሰዓት ከምግብ በፊት ወይንም 2 ሰዓት ከምግብ በኋላ ቆይቶ መመገብ ይቻላል፡፡  ሲጋራን አያጢሱ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከምግብ በኋላ ሲጋራን ማጤስ ለካንስር ተጋላጭነትን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል፡፡ ከምግብ በኃላ ብቻ ሳይሆን ባጠቃላይ ሲጋራ ማጤስ ለጤናዎ ጎጂ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ምግብን በሚመገቡ ጊዜ • በትክክል ተቀምጦ መመገብ • በዝግታ መመገብ • በሚገባ አላምጦ መመገብ • ከጥጋብ በላይ አለመመገብ ያስፈልጋል ከምግብ በኃላ ትንሽ ጊዜ ሰጥተው ቁጭ ብለው እረፍት ማድረግም ይችላሉ (መተኛትን አይጨምርም)፣ ቢያንስ ለሰላሳ ደቂቃ ከላይ የተጠቀሱትን ባያደርጉ ይመከራል። ምንጭ፦በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም 

Advertisement