አንድ በሚስቱ በጣም የተማረረ ባል ሳይኮሎጂስት ጋር ይሄዳል…

                      

አንድ በሚስቱ በጣም የተማረረ ባል ሳይኮሎጂስት ጋር ይሄዳል…

ሳይኮሎጂስት ፡- እሺ ጌታው ለመኖር ምንድ ነው የምትሰራው ?
ባል ፡- ባንክ ቤት ውስጥ ማናጀር ነኝ
ሳይኮሎጂስት ፡- እሺ ባለቤትህስ ምንድ ነው ምትሰራው ?
ባል ፡- እሷ ባክህ ምንም አትሰራም የቤት እመቤት ነች
ይኮሎጂስት ፡- ጠዋት ለቤተሰቡ ቁርስ ሚሰራው ማነው ?

ባል ፡- ሚስቴ ነቻ ምክንያቱም ምንም ስራ የለባትም..
ሳይኮሎጂስት ፡- ሚስትህ ጠዋት ከእንቅልፏ ስንት ሰአት ነው ምትነሳው ?
ባል ፡- ለሊት 11፡00 ሰአት አካባቢ ነው ምትነሳው ቁርስ ከመስራቷ በፊት ቤት ስለምታጸዳ ቀደም ብላ ነው ምትነሳው…..
ሳይኮሎጂስት ፡- ልጆችህ ትምህርት ቤት ሚሄዱት እንዴት ነው ?
ባል ፡- ሚስቴ ስራ ስለሌላት እሷ ነች የምትወስዳቸው
ሳይኮሎጂስት ፡- ልጆችህን ትምህርት ቤት ከወሰደደች በኋላ ምን ትሰራለች ?
ባል ፡- ከወሰደቻቸው በኋላ ያው ስራ ስለሌለባት ወደ ገበያ ሄዳ ምሳ የሚሰራበትን ነገር ትገዛዛና ምሳ ከሰራች በኋላ ልብስ ታጣጥብና እረፍት ታረጋለች በቃ ም
ንም ምትሰራው ስራ የላትም

ሳይኮሎጂስት ፡- አንተ ማታ ከስራ ስትመለስ ምን ታረጋለህ ?
ባል ፡- እኔ ስራ ደክሜ ስለምገባ በቃ ሻወር እወስድና ረጋ ብዬ ከልጆቼ ጋር እቀመጣለሁ
ሳይኮሎጂስት ፡- የዛኔ ሚስትህ ምን ትሰራለች ?
ባል ፡- ለቤተሰቡ ራት ታቀርብና እቃ ታጣጥብና ልጆቹን አስተኝታ ወደ እንቅልፍ ትሄዳለች
ሳይኮሎጂስት ፡-እሺ ከአንተና ከሚስትህ ማን በጣም የሚሰራ ይመስልሃል የሚስትህ ውሎ ከንጋቱ 11 ሰአት የጀመረ እስከ ማታ ድረስ የሚቀጥል ነው፡፡ ታዲያ ይሄንን ነው ስራ ስለሌለባት የምትለው !!!! አዎ በርግጥ የቤት እመቤት ለመሆን ትምህርት ቤት ገብቶ ሰርተፍኬት መቀበል ላያስፈልገው ይችላል፡፡ ግን በሕይወታችን ውስጥ የነሱ አስተዋጽኦ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
Appreciate your wife’s because their sacrifices is uncountable.
ስለ ሴቶቻችን…..
• ፀጥ ስትል ብዙ ሚሊዮን የሚሆኑ ሃሳቦችን እያሰበች እያብሰለሰለች መሆኑን ይግባህ፡፡
• አፍጣ ስታይህ ለምን እንደዚ እንደምትወድህ እና ይህን ሁሉ መስዋትነትን እንደምትከፍልልህ እያሰበች ነው፡፡
• አብሬህ እቆማለው ስትልህ ማዕበል እንኳን ቢመጣ አልንቀሳቀስም ማለቷ ነው፡፡
• አትጉዳት ወይም በተሳሳተ መንገድ አታስባት….አንተ ስትራብ ተርባ ስትቸገር ተቸግራ ስትራቆት ተራቁታ ገበናህን ሸፍና የምትኖረው ሚስትህ የልጆችህ እናት ሚስትህ ናት፡፡ አረ እውነታውን ልንገርህ ሚስትህ ማለት የቤትህ ብርሀን ናት።
ስለዚህ አክብራት ውደዳት ፍቅርን ስጣት፡


ከ FACEBOOK የተገኘ

Advertisement