ተቅማጥ/Diarrehea/

                                                                 

ተቅማት በህክምናው አጠራር ዲሀሪያ ተደጋጋሚ በሆነ ውሃማነት ያለው ሰገራ መታየት፣ማቅለሽለሽ፣የሰውነት ሙቀት መጨመርና የምግብ ፍላጎት መቀነስ በማስከተል ሊከሰት ይችላል;; ተቅማጥ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ/Acute/ ወይም ለረጅም ጊዜ የሚቆይ/Chronic/ እስከ 2 ሳምንት አካባቢ የሚቆይ ሊሆን ይችላል;;
ምልክቶች
-ቁርጠት፣ ሆድ መነፋት 
-ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ
-ደም፣ሙከስ ወይም ያልተፈጨ ምግብ ከሰገራ ጋር መታየት 
-ክብደት መቀነስ 
-ትኩሳት
ጠቃሚ ምክሮች 
-በየቀኑ ከ8-10 ብርጭቆ ፈሳሽ መውሰድ 
-እንደ ሾርባ ያሉ ፈሳሾችን መውሰድ
-ቡና፣ኮላ፣አልኮል፣ቅባታማና ቅመም የበዛባቸውን ምግቦች ተቅማጡ እስከሚቆም አለመውሰድ 
-ማግኔዥየም አብዝተው የያዙ ምግቦችን አለመመገብ 
-ሙዝ መመገብ በሰውነታችን ውስጥ ለኢንፌክሽን ተጋላጭነትን ይቀንሳል::

ምንጭ:- ጤናችን

Advertisement