የአስም በሽታ በመላው ዓለም የሚታይ ሲሆን በአየር ብክለት ምክንያት መጠኑ እየጨመረ ይገኛል።
አስም ያለባት ሴት ማርገዝ ትችላለች ወይ?
አዎን
እርግዝና በአስም ላይ የሚያመጣው ችግር
አስም ካለባቸው ነፍሰ-ጡሮች ውስጥ
· ሲሶዎቹ (1/3)- ከበፊቱ የተለየ ህመም አይታይባቸውም
· ሲሶዎቹ – ይሻላቸዋል
· ሲሶዎቹ – ደግሞ በጣም ይታመማሉ።
በዚህ ምክንያት አስም ያለባት እናት በእርግዝና ጊዜ መድኃኒቷን እንዳታቋርጥ ይመከራል።
አስም በእርግዝና ላይ የሚያመጣው ችግር
አስም ያለባት እናት ከጤነኛዋ በበለጠ
· ለደም ግፊት
· ያለጊዜው መውለድ
· ክብደቱ ትንሽ የሆነ ወይም በማህፀን ውስጥ የቀጨጨ ህፃን
· ሲወለዱ የመታመምና የመሞት እድላቸው ከፍ ያሉ ህፃናትን የመውለድ እድል አላት።
መፍትሄው ፦ አስሙን በተቻለ አቅም እየተቆጣጠሩ ጥሩ የሆነ የእርግዝና ክትትል ማድረግ ይኖርባታል።
ምንጭ፡-ዶ/ር ቤተል ደረጄ