በሴቶች ህይወት ውስጥ አመጋገብ ላይ ትኩረት ሊሰጣቸው ከሚገቡ ጊዜያት ውስጥ ዋነኛው ጡት የሚያጠቡበት ጊዜ ነው፡፡ ምክንያቱ በዚህ ጊዜ እናት ለልጇ ብዙ ጠቃሚ ንጥረነገሮችን ስለምታካፍል ሲሆን በፕሮቲን፣ በካርቦሃይድሬት፣ በጤናማ ስብ እና በሌሎችም የበለፀጉ ምግቦች ያስፈልጓታል ሲሉ የዘርፉ ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡
Live strong በተባለው የመረጃ ምንጭ ላይም ከእነዚህ አስፈላጊ ከሚባሉት ምግቦች ውስጥ ወሳኝ የሚባሉትን ባለሞያዎቹ ጠቁመዋል፡፡
– በካልሺየም የበለፀጉ ምግቦች፡- ወተት፣ ቅጠላ ቅጠሎች እንዲሁም የብርቱካን ጁስ
– ምስር
– አቮካዶ፡- የቫይታሚን C እና የጤናማ ስብ ምንጭ ሲሆን በቂ ሀይል ለማግኘት እንዲሁም የቆዳ መድረቅና መገርጣት እንዳይኖር ህዋሶች እንዲገነቡ ያደርጋል፡፡
– ቅጠላ ቅጠሎች፡- የአበባ ጎመን፣ ስፒናች፣ ጥቅል ጎመን፡፡ እነዚህ በቫይታሚን A፣ C፣ K፣ በካልሺየም፣ አይረን እንዲሁም በፋይበር የበለፀጉ ስለሆኑ በተለይም ህፃኑ 6 ወር ከሆነው በኋላ ጡት በምታጠባ እናት ቢወሰዱ መልካም እንደሆነ ታምኖበታል፡፡
– አይረን እና ቫይታሚን Bን የሚይዘው ሩዝ፣ እንጉዳይ፣ በአዮዲን የበለፀገ ጨው እና እንቁላል (ለቁርስ ሰዓት) ከሚመከሩ የምግብ አይነቶች ውስጥ እንዲካተቱ ተጠቁሟል፡፡
ምንጭ፡ Livestrong.com