የጥቁር አዝሙድ ዘይት የጤና ጥቅሞች – Health Benefits of Black Cumin Oil.

                                                

1. ለካንሰር በሽታ
የክሮሺያ ሳይንቲስቶች በጥቁር አዝሙድ ዘይት ውስጥ ስለሚገኙ ሁለት ፋይቶ ኬሚካሎች እንዴት ካንሰርን እንደሚከላከሉ ጥናት አድርገው ነበር በጥናታቸውም መሠረት እነዚህ በጥቁር አዝሙድ ዘይት ውስጥ የሚገኙ ሁለት ኬሚካሎች (ታይሞኪውኖን እና ታይሞሃይድሮኪውኖን) ካንሰርን የሚያስከትሉ ቲውመር ሴሎችን በ52% መከላከል እንደሚችሉ ማረጋገጥ ችለዋል፡፡ በሁለቱ ኬሚካሎች መበልፀጉ ጥቁር አዝሙድን የተለየ ያደርገዋል ይህም ካንሰርን በተለያዩ መንገዶች ለመከላከል እና ለማከም ይረዳል፡፡
2. ለጉበት ጤንነት
ጉበት ለሰውነታችን በጣም አስፈላጊ ከሆኑ አካሎቻችን አንዱ ነው፡፡ ወደ ሰውነታችን የገባ ማንኛውም መርዛማ ነገር በጉበት አማካይነት ይረክሳል፤ ከጉበት የሚገኝው ሀሞት ስብን(ፋት) በመፍጨት እንዲሁም አእምሮና ሰውነታችን ደስተኛና ጤናማ በማድረግ ቁልፍ የሆነ ሚና በመጫወት ይጠቅመናል፡፡
በመድሃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት፣ በአልኮል መጠጦችና በተለያዩ በሽታዎች ጉበታቸው ለተጎዳ ወይም ስራውን ለቀነሰባቸው ሰዎች የጥቁር አዝሙድ ዘይት ጉበት ለማገገም/ለመዳን የሚያደርገውን ሂደት በሚገርም ሁኔታ ያፋጥናል፡፡
3. ለስኳር በሽታ
በህንድ የህክምና ቡድን ተጠንቶ ለህትመት የበቃው ጥናት እንደሚሳየው የጥቁር አዝሙድ ዘይት የጣፊያ ቤታ ሴሎች በፍጥነት እንዲገግሙ፣ በሴረም ውስጥ ቀንሶ የሚገኝውን የኢንሱሊን መጠን እንዲጨምር እና በሴረም ውስጥ ጨምሮ የሚገኝውን የስኳር መጠን እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ እንደሚታወቀው ኒጌላ ሳቲቫ () በተክሎች ላይ ከሚገኙ ጥቂት ንጥረ ነገሮች ውስጥ አንድ ሲሆን አይነት 1 እና 2 የስኳር ህመሞችን በመከላከል ይረዳናል፡፡
4. የሰውነት ክብደት ለመቀነስ
ፀረ-ውፍረት ባህሪ ያላቸው ተክሎች የትኞቹ እንደሆኑ ለመለየት የተደረገ አንድ ጥናት እንደሚያሳየው የጥቁር አዝሙድ ዘይት ውጤታማ ተፈጥሮአዊ የውፍረት መከላከያ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በሚከተሉት የሰውነት ክብደትን ሊጨምሩ የሚችሉ ክንውኖችን በመግታት ወይም በማስተካከል ይረዳናል፦
• የምግብ ፍላጎት
• ግሉኮስ(ስኳር) አንጀት ውስጥ መመጠጥ
• የደም ስኳር መጠን
• ኮሌስትሮል
• ትራይግላይሴራይድስ
5. ለፀጉር መሳሳት
ከብዙዎቹ አንዱ ልዩ የሆነ የጥቁር አዝሙድ ጥቅም የፀጉር መሳሳትን ወይም መመለጥን መከላከሉና በፍጥነት እንዲገገም ማድረጉ ነው፡፡ ይህ እንዴት እንደሆነ ማንም ማወቅ ባይችልም ለመገመት ግን በጣም ቀላል ነው ይህም ጥቁር አዝሙድ ከፍተኛ የሆነ ፀረ-ኦክሲዳንት እና ፀረ-ባክቴሪያ ባህሪ ስላለው ነው፡፡
6. ቆዳ
ሜላኒን ቀለም ሲሆን ቆዳችን ጉዳት እንዳይደርስበት በመከላከል ይጠቅመናል፡፡ ለአይናችን፣ ቆዳችን እና እያንዳንዳችን የራሳችን ቀለም እንዲኖረን በማድረግ ከፍተኛ የሆነ ሚናን የሚወጣ ኬሚካል ነው፡፡ ከሜላኒን ጋር የተያያዙ የቆዳ በሽታዎች እንዲያገግሙ ይረዳናል፡፡
7. ኢንፌክሽን
አለም አቀፍ ስርጭት ያለውንና ሜቲሲሊን ረዚስታንት ወይም በሜቲሲሊን የማይሞተው ስታፋሎኮከስ አውረስ (Staphylococcus aureus) የሚባለውን ባክቴሪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በመግደልና በማጥፋት ይጠቅመናል፡፡

ምንጭ:- ጤናችን

Advertisement