ጥሩ አባት መሆን የምትችልባቸው 4 ዘዴዎች

በደቡብ አፍሪካ የሚኖረው ማይክል * “የተሳሳትኩት ነገር ምንድን ነው?” የሚለው ጥያቄ እረፍት ይነሳዋል። ጥሩ አባት ለመሆን ብዙ ቢያደርግም ዓመፀኛ ስለሆነው የ19 ዓመት ልጁ ባሰበ ቁጥር የተሻለ አባት መሆን ይችል እንደነበረ ይሰማዋል።

በተቃራኒው በስፔን የሚኖረው ቴሪ ደግሞ የአባትነት ኃላፊነቱን በመወጣት ረገድ የተሳካለት ይመስላል። ልጁ አንድሩ እንዲህ ብሏል፦ “ስለ አባቴ ያለኝ የልጅነት ትዝታ ደስ የሚል ነው፤ ሲያነብልኝ፣ ሲያጫውተኝ እንዲሁም ለብቻችን ጊዜ ለማሳለፍ እንድንችል ወደተለያዩ ቦታዎች ሲወስደኝ ትዝ ይለኛል። በጨዋታ መልክ ያስተምረኝ ነበር።”

ጥሩ አባት መሆን ቀላል ነገር እንዳልሆነ አይካድም። ጥሩ አባት ለመሆን የሚከተሉትን ተግባራዊ አድርጉ
1. ለቤተሰባችሁ ጊዜ ስጡ

አባት እንደመሆናችሁ መጠን ልጆቻችሁ በእናንተ ዘንድ ትልቅ ቦታ እንዳላቸው ማሳየት የምትችሉት እንዴት ነው? ለልጆቻችሁ ምግብና መጠለያ ለማቅረብ የምትከፍሉትን መሥዋዕትነት ጨምሮ በርካታ ነገሮች እንደምታደርጉላቸው የታወቀ ነው። ልጆቻችሁ በእናንተ ዘንድ ትልቅ ቦታ ባይኖራቸው ኖሮ እነዚህን ነገሮች አታደርጉም ነበር። ይሁን እንጂ ከልጆቻችሁ ጋር በቂ ጊዜ የማታሳልፉ ከሆነ ከእነሱ ይልቅ ለሥራችሁ፣ ለጓደኞቻችሁ፣ በትርፍ ጊዜ ለምትሠሯቸው ነገሮችና ለመሳሰሉት ትልቅ ቦታ እንደምትሰጡ ሊያስቡ ይችላሉ።
አንድ አባት ከልጆቹ ጋር ጊዜ ማሳለፍ መጀመር የሚኖርበት መቼ ነው? እናት ከልጇ ጋር ትስስር መፍጠር የምትጀምረው ልጁ ገና ማህፀን ውስጥ እያለ ነው። አንድ ጽንስ በ16 ሳምንታት ውስጥ መስማት ይጀምራል። በዚህ ጊዜ ውስጥ አባትም ቢሆን ካልተወለደው ልጁ ጋር ልዩ የሆነ ዝምድና መመሥረት ይችላል። በዚህ ወቅት አባትየው የልጁን የልብ ትርታ ሊያዳምጥ፣ ልጁ ሲንፈራገጥ ሊሰማው፣ ሊያወራለትና ሊጫወትለት ይችላል።

2. ጥሩ አባቶች ጥሩ አዳማጮች ናቸው
ልጃችሁ ላይ ሳትፈርዱ በእርጋታ አዳምጡ
ከልጆቻችሁ ጋር ጥሩ የሐሳብ ልውውጥ ለማድረግ ጥሩ አድማጭ መሆን ያስፈልጋችኋል። ሳትደናገጡ ወይም ሳትቆጡ ማዳመጥ መቻል ይኖርባችኋል።
በቁጣ ቶሎ የምትገነፍሉ ከሆነ አሊያም በልጆቻችሁ ላይ የመፍረድ አዝማሚያ ካላችሁ የውስጣቸውን አውጥተው ለእናንተ የመናገር ፍላጎት አይኖራቸውም። በእርጋታ የምታዳምጧቸው ከሆነ ግን ከልብ እንደምታስቡላቸው ማየት ይችላሉ። ይህ ደግሞ የውስጣቸውን አውጥተው እንዲናገሩ ያነሳሳቸዋል።

3. ፍቅራዊ ተግሣጽ ስጧቸው እንዲሁም አመስግኗቸው
በምታዝኑበት ወይም በምትቆጡበት ጊዜ እንኳ የምትሰጡት ተግሣጽ ለልጃችሁ ዘላቂ ጥቅም እንደምታስቡ የሚያሳይ መሆን አለበት። ተግሣጽ ሲባል ምክርን፣ እርማትንና ትምህርትን አስፈላጊ ሲሆን ደግሞ ቅጣትን ያካትታል።
በሌላ በኩል ደግሞ ተግሣጽ ይበልጥ ውጤታማ የሚሆነው አባት ልጆቹን አዘውትሮ የሚያመሰግን ከሆነ ነው። በጥንት ጊዜ የተነገረ አንድ ምሳሌ “ባግባቡ የተነገረ ቃል፣ በብር መደብ ላይ እንደ ተቀረጸ የወርቅ እንኮይ ነው” ይላል። ምስጋና አንድ ልጅ ጥሩ ባሕርያትን እንዲያፈራ ያደርገዋል። ልጆች በራስ የመተማመን መንፈስ እንዲኖራቸው እውቅና ሊሰጣቸው አልፎ ተርፎም አድናቆት ሊቸራቸው ይገባል። ልጆቹን ለማመስገን አጋጣሚዎችን በንቃት የሚከታተል አባት ልጆቹ በራስ የመተማመን መንፈስ እንዲያዳብሩና ትክክል የሆነውን ነገር ከማድረግ ወደኋላ እንዳይሉ ይረዳቸዋል።

4. ለትዳር ጓደኛችሁ ፍቅርና አክብሮት ይኑራችሁ
አንድ አባት ሚስቱን የሚይዝበት መንገድ ልጆቹ ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ አይቀርም። ስለ ልጆች አስተዳደግ የሚያጠና አንድ የባለሙያዎች ቡድን እንዲህ ብሏል፦ “አንድ አባት ለልጆቹ ሊያደርግ ከሚችላቸው ጥሩ ነገሮች አንዱ እናታቸውን ማክበር ነው። . . . እርስ በርሳቸው የሚከባበሩና ለልጆቻቸው ይህን የሚያሳዩ ወላጆች ልጆቻቸው ደስተኛ እንዲሆኑ እንዲሁም እንደሚወደዱ እንዲሰማቸው ያደርጋሉ።”—ዚ ኢምፖርታንስ ኦቭ ፋዘርስ ኢን ዘ ሄልዚ ዴቨሎፕመንት ኦቭ ችልድረን *

ስለ አባት ….ከተነገሩ
የባርቤዶስ ተወላጅ የሆነው ሲልቫን የሚኖረው ከሚስቱና በአሥራዎቹ ዕድሜ ከሚገኙ ሦስት ልጆቹ ጋር ነው። ሲልቫን በኒው ዮርክ ሲቲ ውስጥ የከተማ አውቶቡስ ሾፌር ስለሆነ የሥራ ፕሮግራሙ በጣም አስቸጋሪ ነው። ከሰዓት ወደ ዘጠኝ ሰዓት ገደማ ጀምሮ እስከ ሌሊቱ ዘጠኝና አሥር ሰዓት ድረስ ይሠራል። ሐሙስና ዓርብ እረፍት ቢኖረውም ቅዳሜና እሁድ ምሽት ላይ ይሠራል። ያም ቢሆን ሲልቫን ለልጆቹ የሚሆን ጊዜ አያጣም።
ሲልቫን እንዲህ ብሏል፦ “በጣም ከባድ ቢሆንም የቻልኩትን አደርጋለሁ። ሁሉም ልጆቼ ከእኔ ጋር ብቻቸውን የሚያሳልፉት ጊዜ ያስፈልጋቸዋል። ሐሙስ ከሰዓት በኋላ ትልቁ ልጄ ከትምህርት ቤት ሲመለስ ከእሱ ጋር ጊዜ አሳልፋለሁ። ዓርብ ከመካከለኛው ልጄ ጋር እሁድ ጠዋት ደግሞ ከትንሹ ልጄ ጋር እሆናለሁ።” ብሏል .. አባት መቼም ቢሆን ለልጆቹ ጊዜ ማጣት የለበትም 

ምንጭ: አድማስ ሬዲዮ አትላንታ

Advertisement

6 Comments

Comments are closed.