በማንኛውም መጠን የሚወሰድ የአልኮል መጠጥ የስትሮክ ተጋላጭነተን ይጨምራል

በማንኛውም መጠን የሚወሰድ አልኮል የደም ግፊትን ከፍ በማድረግ የስትሮክ ወይም ወደ ጭንቅላት ሊደርስ የሚገባው የደም ፍሰት መቀነስ ወይም መቋረጥ ተጋላጭነትን ከፍ እንደሚያደርግ አዲስ ጥናት አመላክቷል።

የብሪታኒያ እና የቻይና ተመራማሪዎች በ500 ሺህ ቻይናውያን ላይ ለ10 ዓመታት ያካሄዱትን ጥናት ተከትሎ ያገኙትን ውጤት ከሰሞኑ ይፋ አድርገዋል።

እንደ ተመራማሪዎቹ ገለፃ በቀን አንድ ብርጭቆ እንኳ የአልኮም መጠጥን መጠጣት ለስትሮክ ወይም ወደ ጭንቅላት ሊደርስ የሚገባው የደም ፍሰት መቀነስ ወይም መቋረጥ የመጋለጥ እድልን ከፍ ያደርጋል።

እንደ ተመራማሪዎቹ ገለጻ፦

  • በቀን አንድ እስከ ሁለት ብርጭቆ አልኮል መጠጣት ለስትሮክ የመጋለጥ እድልን ከ10 እስከ 15 በመቶ ከፍ ያደርጋል።
  • በቀን አራት ብርጭቆ የአልኮል መጠጥ መጠጣት ለስትሮክ የመጋለጥ እድልን በ35 በመቶ ከፍ ያደርጋል።

ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ፣ ከፔኪንግ ዩኒቨርሲቲ እና ከቻይና ሜዲካል አካዳሚ የተውጣጡት ተመራማሪዎች እንዳስታወቁት ከሆነ፥ ሰዎች ጤናቸውን ለመጠበቅ ሲባል ከመጠጥ ቢርቁ አሊያም የአልኮል አወሳሰዳቸውን ቢገድቡ መልካም ነው ብለዋል።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

2 Comments

Comments are closed.