አይን ማሳከክ ሁላችንንም በህይወታችን የሚያጋጥመን ህመም ነው። እልህ አስጭራሽ እና አታካች ደረጃም ሊደርስ ይችላል።
ከማሳከክ አልፎም አይንን የማቃጠል፣ ውሃ የመቋጠር፣ የመቅላት እና የፍሳሽ ችግሮች አብረውት ይታያሉ። ብርሃን ለማየት መቸገርም ሊመጣ ይችላል።
አብዛኛው ግዜ የማሳከክ መንስኤው አልርጂ እና ኢንፌክሽን ናቸው። ደረቅ አይን፣ ኮንታክት ሌንስ፣ የአይን ንጽህና መጓደልም መነሻ ይሆናሉ።
አይናቸውን በእጃቸው በሚነኩ ሰዎች ላይ ችግሩ ይበልጥ ይታያል። የማሳከክ ስሜቱ በተበከለ አካባቢ እና አየር በሚለዋወጥበት ወቅት ሲባባስ ይታያል።
አይን የማሳከክ ስሜትን በፍጥነት መፍትሄ ካልተበጀለት ወደ ኮምፕሊኬሽን ሊያመራ ይችላል። በአይን ላይ ዘላቂ ጉዳት የማድረስ ስጋት አለው።
ህመሙን ለማስታገስ ቤት ውስጥ ልናደርጋቸው የምንችለው 10 ነገሮች እነሆ።(ህመሙ ለውጥ ካላሰየ ግን በፍጥነት የአይን ሃኪም ሂደው እንዲታዩ እንመክራለን።)
ቀዝቃዛ በረዶ
ቀዝቃዛ በረዶ በጨርቅ ጠቅልለው የሚያሳክክዎት አይን ክዳን ላይ ማድረግ ስሜቱን ይቀንሰዋል። ጨርቁ ለስላሳ እና ንጹህ መሆን አለበት። ይህ መፍትሄ በአለርጂ ምክንያት ለመጣ ማሳከክ ይረዳል።
ለአይን መድረቅና የመጠዝጠዝ ስሜት ሲኖር የሚረዳ መፍትሄ ነው። ጨርቁን አይንዎት ላይ ከ5-10 ደቂቃ እንዲያደርጉ ይመከራል። ከ2-3 ጊዜ መደጋገም በቂ ነው።
በረዶ ካልተገኘ ጨርቁን ቀዝቃዛ ውሃ ውስጥ ነክረው የጭመቁና አይንዎ ላይ ያድርጉ።
ካሞሜል
ካሞሜል ሻይ ለአለርጂ የሚረዳ ንጥረ ነገር አለው። በካሞሜል አይን መታጠብ የህመሙን ስሜት ለመቀነስ ይረዳል። ካሞሜል ሂስታሚን የሚባለውን ኬሚካል ከሰውነታችን የሚወጣበትን ፍጥነት ይቀንሳል። በማድረግም የአለርጂክ ቁጣ እንዳይኖረን ይረዳል.
ካሞሜልን ለአይን በሁለት መንገድ ማድረግ ይቻላል።
– ካሞሜል ቅጠሉን የፈላ ውሃ ውስጥ ለ5 ደቂቃ ይንከሩ። ከዛ ቅጠሉን ያውጡና ሻዩ እስኪቀዘቅዝ ይጠብቁ። በቀዘቀዘው ሻይ አይንዎን ይጠቡት። በቀን 2 ወይም 3 ግዜ ማድረግ ይመከራል።
– የካሞሜል ቅጠሉን ፍሪጅ ውስጥ ከተው ያቅዝቅዙት። የቀዘቀዘውን ቅጠል የተጨፈነው አይን ላይ ለ10 ደቂቃ ያድርጉ። በቀን 3 ወይም 4 ግዜ ማድረግ ይመከራል።
ዝኩኒ
ዝኩኒ መጠዝጠዝን የሚረዳ እና አንቲኦክሲዳንት ንጥረ ነገር አለው። ለአይን ማቃጠል እና መጠዝጠዝ የሚረዳ አትክልት ነው።
ዝኩኒውን በደንብ ካጠቡ በኋላ በቀጭኑ ይክተፉት። የከተፉትን ዝኩኒ ፍሪጅ ውስጥ ከ15 እስከ 20 ደቂቃ ያድርጉ። አውጥተው ቁርጥራጩን በጨፈኑት አይን ላይ ለ10 ደቂቃ ያድርጉ። በቀን ከ4 እስከ 5 ግዜ ማድረግ ይመከራል።
ቀዝቃዛ ወተት
ቀዝቃዛ ወተት አይንዎት ላይ ለሚሰማዎት የማቃጠል ስሜት ይረዳል።
ንጹህ ጥጥ በቀዝቃዛ ወተት ውስጥ ይንከሩና በተዘጋ አይንዎት ላይ ቀስ ብለው ይሹት። በቀን ሁለት ግዜ እንዲያደርጉት ይመከራል። ጧት እንዴ ማታ እንዴ። ማሸት ካልፈለጉ ጥጡን አይንዎት ላይ ከ15-20 ደቂቃ ማስቀመት ይችላሉ።
አረንጓዴ ሻይ
1 ብርጭቆ የፈላ ውሃ ውስጥ ሁለት አረንጓዴ ሻይ ቅጠል ከተው 5 ደቂቃ ያቆዩ። ቅጠሉን አውጥተው እስኪቀዘቅዝ ይጠብቁ። አይንዎትን ይጠቡበት። በቀን ሁለት ግዜ እንዲያደርጉ ይመከራል። እንደ አማራጭ የቀዘቀዘውን ሻይ ቅጠል አይንዎት ላይ ለተወሰነ ደቂቃ ማድረግ ይችላሉ።
ጨው
አይንዎን በጨው ማጠብ በአለርጂ ወይም በአቧራ የሚከሰትን ማሳከክ ይቀንሳል። የጨው ውህድ አይንዎ ላይ ያለ ቆሻሻ ያጸዳል ባክቴሪያዎችንም ይገላል።
መጀመርያ 1 ንኬል ውሃ ያፍሉ። እስኪቀዘቅዝ ይጠብቁና 1 የሻይ ማንኪያ ጨው ይጨምሩበት። በደንብ ያማስሉና አይንዎን ይጠቡበት። ካልሆነ ጥጥ ነክረው አይንዎን መዳበስ ይችላሉ። በቀን ሁለት ሶስት ግዜ ማድረግ ይመከራል።
እሬት(Aloe Vera)
እሬት ሌላ የቅባት ይዘት ያለው አትክልት ነው። እሬት ውስጥ ያለው ንጥረ ነገር ለአይን ማቃጠል ስሜት ህክምና ይውላል።
የእሬት ቅጠሉን በደንብ ይጠቡና በቢላዋ ልጠው ውስጥ ያለውን ቅባት ያውጡ። ቅባቱን አይንዎ ክዳን ላይ በመቀባት ለ15-20 ደቂቃ ያውሉ። እንዳስፈላጉነቱ በቀን ሁለት ግዜ ማድረግ ይችላሉ። እንዳማራጭ ፍሳሹን በጥጥ አንስተው አይንዎን ለ15 ደቂቃ መዳሰስ ይችላሉ።
የጉሎ ዘይት (Castor Oil)
የጉሎ ዘይት የልስላሴ ንጥረ ነገር ያለው ዘይት ነው። ደረቅ እና የሚያሳክክ አይን ለማከም ይረዳል። በተጨማሪም በውስጡ ጸረ-ቃጠሎ እና ጸረ-ባክቴሪያ ንጥረ ነገሮች አሉት። የአይን ኢንፌክሽን ለማከም ይረዳል።
ጠቃሚ መረጃዎችን እናቀርባለን ፤ እንወያያለን እንዲሁም ለሚነሱ ጥቅዎች ሞያዊ ምላሽ እንሰጣለን ፡፡
በማንኛውም የጤና ጉዳይ ባለሙያ ማማከር ከፈለጉ
የዶክተር አለ 8809 ሀኪሞችን ላይ እየደወሉ የየዕለቱን የጤና ላይ ለውጦችዎን በማማከር ነገ ከሚከሰት የጤና ችግር አስቀድመው ራስዎንና ቤተሰብዎን ይጠብቁ ይንከባከቡ::
ምንጭ: ዶክተር አለ (Doctor Alle)
excellent product with premium package
get credit score credit scores fico credit score
business credit score free credit score check credit score ratings credit score simulator [url=http://creditscorechecknw.com/# ]credit check [/url]
slots for real money no deposit casino casino game free casino [url=http://casinoslotscnm.com/# ]slots for real money [/url]
Nearby the ICI libido is not recommended nigh your regional mettle, you should. cheap sildenafil online Cggtlc pvvcao
cbd pills hemp cbd cbd oil for sale