ህፃናት ጤናማ ሆነው መቆየት እንዲችሉ ትኩስና ጤናማ ምግብ እንዲያዘወትሩ ቢመከርም ህፃናቱ ለእንደዚህ አይነት ምግቦች ያላቸው ፍላጎት ዝቅተኛ መሆኑን ያመላክታሉ።
በመሆኑም ልጆች ጤናማ ሆነው እንዲያድጉ ትክክለኛውንና አስፈላጊውን የምግብ ይዘት መመገባቸውን ቤተሰቦቻቸው ሊከታተሉ እንደሚገባ ይነገራል፡፡
በተለይ ህጻናት በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦችን እንዳይመገቡ ማድረግና በቫይታሚን፣ ማዕድናት እና በንጥረ ነገሮች የበለፀጉ ምግቦችን እንዲያዘወትሩ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ባለሙያዎች ይገልፃሉ፡፡
ለህፃናት ጤና አፈላጊ የሆኑ ምግቦች፤
1.እንቁላል
እንቁላል በፕሮቲንና ለህጻናት የአዕምሮ እድገት የሚረዳው ዲ ኤች ኤ ንጥረ ነገር የበለጸገ በመሆኑ እጅግ አስፈላጊ ነው።
2.አሳ
በተለይ በጨዋማ ባህር የሚገኙ አሳዎች በህጻናት ተመራጭ ባይሆኑም አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን የያዙ ናቸው።
በመሆኑም ከሩዝና ሌሎች ነገሮች ጋር እየቀላቀሉ ለህፃናት ማቅረብ አስፈላጊ ነው።
3.ጥራጥሬ
የበሰለ ባቄላ፣ ጥቁር ባቄላ፣ አተር እና ሌሎች የጥራጥሬ አይነቶች እንዲመመገቡ በማድረግ ፕሮቲን እንዲያገኙ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡
4.የወተት ተዋፅኦ
የላም ወተት በፕሮቲንና ካልሺየም የበለፀገ በመሆኑ ለህጻናት በእጅጉ አስፈላጊ ነው፡፡
በመሆኑም ህፃናት ብሩህ አዕምሮ ይዘው እንዲያድጉ ከሁለት አመት እድሜያቸው ጀምሮ ሁሉንም ወተት መጠጣት ይገባቸዋል።
5.አትክልትና ፍራፍሬ
ፍራፍሬ በተፈጥሮው ጣፋጭና በህፃናት ዘንድ ተወዳጅ የሆነ ምግብ መሆኑ ይታወቃል በመሆኑም ህጻናት በየቀኑ ፍራፍሬ እንዲመገቡ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡
በተለይ ፍራፍሬዎችን በፀሀይና በሌሎች ተፈጥሯዊ መንገዶች በማድረቅ ከተለያዩ ምግቦች ጋር ለህፃናቱ ማቅረብ ይመከራል፡፡
ይህም ህፃናቱ የተመጣጠ ምግብ እንዲያገኙ፣ ከልክ ላለፈ ውፍረት እንዳይጋለጡና የተስተካከለ የስርዓተ ምግብ መፈጨት ስነ ስርዓት እንዲኖራቸው ያስችላል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ስኳር ድንች፣ ከንፁህ ስንዴ የሚዘጋጁ ምግቦችን ከፍራፍሬ እና ከወተት ተዋጽኦ ጋር መስጠቱ፥ ለህጻናቱ አስፈላጊ መሆኑንም ባለሙያዎች ይመክራሉ።
ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)
Вам перевод 154054 руб. https://tinyurl.com/Peaplews NMVVmagazine.planetethiopia.comRKKF
check credit score credit score ratings chart max credit score credit score ranges
slots for real money best online casino play casino online casino real money [url=http://casinogamescbe.com/# ]free casino slot games [/url]
minimum credit score for mortgage how to check my credit score credit score companies
To doff a finicky uninjured with held, in septic and treatment management. cheap sildenafil online canadian pharmacy Dqoytx gtmtya
buy cbd oil cbd hemp best cbd oil cbd oil at walmart