በአካላዊ ቅጣት ካደጉ ሕፃናት ይልቅ ያለ አካላዊ ቅጣት ያደጉት በሥነ-ምግባር የተሻሉ ናቸው

በአካላዊ ቅጣት ካደጉ ሕፃናት ይልቅ ያለ ቅጣት ያደጉት በወጣትነት ዕድሜ ክልል ላይ የተሻለ ሥነ-ምግባር  እንደሚኖራቸው  ተገለፀ፡፡

በዓለማችን የተለያዩ ሀገራት ውስጥ የሚኖሩ ወላጆች ልጆቻቸው ጥሩ ሥነ ምግባር ያላቸውና እራሳቸውን  ፣ቤተሰቦቻቸውን እንዲሁም ሀገራቸውን  የሚጠቅሙ ዜጎች እንዲሆኑ ይፈልጋሉ፡፡

ይህ አላማ ይሳካ ዘንድም ማንኛውም ወላጅ ልጁን የሚያሳድግበት የራሱ የሆነ አካሄድ ይከተላል፡፡

በአንዳንድ ሀገሮች ወላጆች ልጆቻቸውን በስነ- ምግባር ኮትኩቶ ለማሳደግ አካላዊ ቅጣት አስፈላጊ ነው ብለው ያምናሉ፡፡ በሌሎች ሀገሮች ደግሞ በሕፃናትን ላይ አካላዊ ቅጣት ማድረስ የተከለከለ ከመሆኑም በላይ በህግ ሊያስጠይቅ ይችላል፡፡

ሰሞኑን የወጣት ጥናትም በአካላዊ ቅጣት ካደጉ ሕፃናት ይልቅ አካላዊ ቅጣት በተከለከለበት ሀገር የሚያድጉ ህፃናት በወጣትነት ዕድሜ ክልላቸው ላይ የተሻለ ሥነ-ምግባር እንደሚኖራቸዉ ያሳያል፡፡

በኤም ሲ ጊል ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው ጥናት መሰረት ፥ አካላዊ ቅጣት በሚደረግባቸው ሀገራት ያደጉ ህፃናት አካላዊ ቅጣት በተከለከለባቸው ሀገራት ያደጉ ሕፃናት በበለጠ በወጣነት ዘመናቸዉ ነውጠኛ እንደሚሆኑ ያስረዳል፡፡

በተደረገው  የናሙና ጥናትም አካላዊ ቅጣት በተከለከለበት ሀገር ውስጥ የሚያድጉ ወንድ ወጣቶች በ31 % ፥ በቅጣት ካደጉ ወጣቶች የተሻለ ሥነ- ምግባር  አላቸው፡፡በአካላዊ ቅጣት ያላደጉ ሴት ወጣቶች ደግሞ በ45% በቅጣት ካደጉት ጋር ሲነፃፃር የተሻለ ሥነ-ምግባር ይኖራቸዋል፡፡

ሰለሆነም ልጆችን በአካላዊ ቅጣት ከማሳደግ ይልቅ ትክክለኛውን የስነ- ምግባር አካሄድ በማሳየት ማሳደግ ፥ ልጆች በወጣትነት ዘመናቸው ጥሩ ስነ- ምግባር የተላበሱ ዜጎች እንዲሆኑ የሚያስችል መሆኑን ጥናቱ ያመላክታል፡፡

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.