ፎቢያ ማለት ከልክ ያለፈና ጤነኛ ያልሆነ ፍርሀት ማለት ነው። ብዙ ጊዜ ሰዎች ፎቢያ የሚኖራቸው እነሱ የሚያስቡትን ያህል ጉዳት ለማያመጣ ነገር ነው። ለምሳሌ የከፍታ ፎቢያ፣ የነፍሳት ፎቢያ፣ የመርፌ ፎብያ የሚጠቀሱ ናቸው።
ብዙ ጊዜ ፎቢያ በልጅነት ጊዜ የሚፈጠር ቢሆንም ካደግን በኋላም ሊፈጠርብን ይችላል። ፎብያ ያለባቸው ሰዎች ብዙ ጊዜ ፍርሀታቸው ምክንያታዊ እንዳልሆነ ቢረዱም ፍርሀታቸውን ግን መቆጣጠር አይችሉም።
ገና ስለሚፈሩት ነገር ማሰብ ሲጀምሩ ፍርሀትና ጭንቀት ይሰማቸዋል። ፎቢያ ያለባቸው ሰዎች ከሚፈሩት ነገር ለመራቅ የህይወት ዘይቤያቸውን እስከመቀየር ድረስ ሊደርሱ ይችላሉ።
የፎቢያ አይነቶች በአጠቃላይ አራት የፎቢያ አይነቶች ያሉ ሲሆን እነሱም፦
1. የእንስሳት ፎቢያ: ለምሳሌ የእባብ፣ የሸረሪት፣ የአይጥ ፎቢያ
2. የተፈጥሮ አከባቢዎች ፎቢያ: ለምሳሌ የከፍታ፣ የመብረቅ፣ የውሀ እንዲሁም የጨለማ ፎቢያ
3. የሁኔታዎች ፎቢያ: የተዘጉ ቦታዎች ፎቢያ፣ መኪና የመንዳት ፎቢያ፣ በአውሮፕላን የመጓዝ ፎቢያ
4. የህመም እና የደም ፎቢያ: የደም፣ የጉዳት፣ የመርፌ ፎቢያ ናቸው።
የሚከተሉት ደግሞ አስገራሚ የፎቢያ አይነቶች ይመልከቱ።
– አብሉቶፎቢያ፦ ገላን የመታጠብ ፍርሀት
-አሊውሞፎቢያ፦ የነጭ ሽንኩርት ፍርሀት
-አውቶማይሶፎብያ፦የመቆሸሽ (ንፁህ ያለመሆን) ፍርሀት
-ካቶፕትሮፎብያ፦ የመስታወት ፍርሀት
-ዲዳስካሌይኖፎብያ፦ ትምህርት ቤት የመሄድ ፍርሀት
-ድሮሞፎቢያ፦ መንገድ የመሻገር ፍርሀት
-ጋሞፎብያ፦ የጋብቻ (የማግባት) ፍርሀት
-ጌራስኮ ፎቢያ፦ የማርጀት ፍርሀት
-ፊሎፎቢያ፦ በፍቅር የመያዝ ፍርሀት
-ሳይቶፎቢያ፦ የምግብ ፍርሀት
-ዩሮፎብያ፦ የሽንት ወይም ሽንት የመሽናት ፍርሀት
-ባይብሎፎብያ፦ የመፅሀፍት ፍርሀት
ምንጭ: ዶክተር አለ(Doctor Alle)
and that precludes me to you. sildenafil online prescription free Fpsgqb swqxxs