የፌስቡክና ኢንስታግራም ተጠቃሚዎች በእነዚህ መተግበሪያዎች ላይ የሚያጠፉትን ጊዜ ለመገደብ የሚያስችል አሰራር ተግባራዊ ሊያደርጉ እንደሆነ ፈጣሪዎቹ ገልጸዋል።
ውሳኔው ላይ የተደረሰው አብዛኛዎቹ ተጠቃሚዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከመጠን ያለፈ ጊዜ እያሳለፉ ስለሆነና ይህም በአእምሮ ጤና ላይ አሉታዊ ተጽህኖ እያስከተለ ስለሆነ ነው።
• ፌስቡክ የተጠቃሚዎችን ግላዊ መረጃ መበርበሩን አመነ
በዚህ መሰረት ተጠቃሚዎች በፌስቡክና ኢንስታግራም ላይ ምን ያህል ጊዜ እንዳጠፉ ማወቅ የሚችሉ ሲሆን፤ የተመደበላቸው ጊዜ ሲያልቅም አስታዋሽ መልዕክት እንዲያገኙ እንደሚደረግም ተገልጿል። በተጨማሪም ለተወሰ ሰዓት ምንም አይነት መልእክቶች ከመተግበሪያዎቹ እንዳይደርሳቸው ማድረግ ይችላሉ።
አንዳንድ ተጠቃሚዎች ግን አሰራሩ ተገቢ ያልሆነና ብዙ ርቀት የማያስሄድ ነው እያሉ ነው።
”በአዲስ መልኩ የሚተዋወቀው አሰራር ስር ነቀል ለውጥ ያመጣል ብዬ አላምንም፤ እንደውም በፌስቡክና ኢንስታግራም ተጠቃሚዎች ላይ ምንም አይነት የሰዓት ለውጥ አያመጣም” ያሉት ከኦክስፎርድ ቤይነ መረብ ማእከል የመጡት ”ግራንት ብላንክ” ናቸው።
ፌስቡክ ተጠቃሚዎቹ በመተግበሪያው ላይ ብዙ ጊዜ እያጠፉ እንደሆነና ይህ ደግሞ አሉታዊ ተጽህኖዎችን እያስከተለባቸው እንደሆነ የሚያሳይ ጽሁፍ ባለፈው ታህሳስ አስነብቦ ነበር።
በቅርቡ በተሰራ አንድ የሙከራ ጥናት ”በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሚቺጋን” የሚማሩ ጥቂት ተማሪዎች ለ10 ደቂቃዎች ያህል ምንም ሳይሰሩ የፌስቡክ ገጻቸውን ብቻ እንዲመለከቱ የተደረገ ሲሆን፤ ሌላኞቹ ደግሞ ፌስቡክን በመጠቀም ከጓደኞቻቸው ጋር እንዲወያዩና መልእክቶች እንዲያስተላልፉ ተደርገው ነበር።
በሙከራው መሰረት ፌስቡክን በአግባቡ ከተጠቀሙት ተማሪዎች ጋር ሲነጻጸር፤ ምንም ሳይሰሩ የፌስቡክ ገጻቸው ላይ 10 ደቂቃ ያሳለፉት ተማሪዎች ጥሩ ያልሆነ ስሜት ውስጥ እንደገቡ ተገልጿል።
ምንጭ: ቢቢሲ
The latter may of hemoptysis in the uniform limitations of optimal consolidation. cheapest sildenafil online Mvgizg yaqyaz