የቫይታሚን ዲ እጥረት – Vitamin D Deficiency

                                                                                

ቫይታሚን ዲ በሽታ የመከላከል አቅምን ለማሳደግ፣ የህዋሳት እድገትን ለማፋጠን እና ለአጥንት ጥንካሬ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው።
እንደ ታይፕ 1 እና ታይፕ 2 የስኳር በሽታ፣ ከፍተኛ የደም ግፊት እና መሰል በሽታዎችን ለመከላከል እና ለማከምም ከፍተኛ ሚና እንዳለው ጥናቶች ያመለክታሉ።
በፀሀይ ብርሃን አማካኝነት በሰውነታችን ውስጥ የሚመረተው ቫይታሚን ዲ ከተለያዩ ምግቦችም ይገኛል።
እድሜያቸው ከ50 በላይ የሆኑና ለረጅም ጊዜ የፀሃይ ብርሃን በማይገኝበት ስፍራ የሚኖሩ ሰዎች ለቫይታሚን ዲ እጥረት የተጋለጡ ናቸው።
ለቫይታሚን ዲ እጥረት ከተጋለጥን ሰውነታችን ስራውን በአግባቡ መከወን ይሳነዋል፤ በመሆኑም የፀሃይ ብርሃን በማግኘት እና አመጋገባችን በማስተካከል ቫይታሚን ዲ ማግኘት እንችላለን።
በየቀኑ ለ15 ደቂቃ በጠዋት ፀሀይ መሞቅ፣ እንደ አሳ፣ እንቁላል፣ ስጋ እና የጥራጥሬ ምርቶችን መመገብ የቫይታሚን ዲ ማግኛ ሁነኛ መንገዶች ናቸው።
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ነጥቦችም ለቫይታሚን ዲ እጥረት መጋለጣችን ያሳያሉ ተብሏል።
1. የማየት አቅም መቀነስ
ለቫይታሚን ዲ መጋለጣችን ከሚያሳዩ ምልክቶች ውስጥ የማየት አቅም መቀነስ ዋነኛው ነው።
2. የአጥንት እና ጡንቻ ህመም
የቫይታሚን ዲ እጥረት ለአጥንት፣ ጡንቻ እና መገጣጠሚያዎች ህመም ሊያጋልጥ እንደሚችል መረጃዎች ያመለክታሉ።
3. ድካም እና አቅም ማጣት
ሰውነታችን ሀይል ለማግኘት ቫይታሚን ዲ ይፈልጋል፤ በመሆኑም የቫይታሚን ዲ እጥረት ለከፍተኛ ድካም ያጋልጣል።
የዚህ ቫይታሚን እጥረት የስብ ክምችት እንዲጨምር በማድረግ የምግብ መፈጨት ሂደትን ያዘገያል፤ ይህም ሀይል እና ብርታትን ያሳጣል።
4. ጥሩ ያልሆነ ስሜት
የፀሃይ ብርሃን እጥረት ድንገተኛ የሆነ የስሜት መቀያየርን ሊያስከትል ይችላል።
ቫይታሚን ዲ ጥሩ ስሜት የሚፈጥረው የአዕምሮ ሆርሞን (ሴሮቶኒን) መመረትን ያፋጥናል።
የሴሮቶኒን በብዛት መመረት ከጭንቀት እና ውጥረት ለመውጣት ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል።
በመሆኑም ለቫይታሚን ዲ እጥረት መጋለጥ ጥሩ ያልሆነ ስሜት እንዲሰማን ምክንያት እንደሚሆን ነው የተነገረው።
5. የቆዳ በሽታ
የቫይታሚን ዲ እጥረት ለቆዳ ቀለም መቀየር እና ቆዳ ላይ ለሚወጡ ቁስሎች መፈጠር ምክንያት የመሆን እድል እንዳለውም ነው የተነገረው።
6. የምግብ መፈጨት ችግር
7. ከፍተኛ ላብ
በሰውነታችን ውስጥ በቂ ቫይታሚን ዲ ከሌለ ከፍተኛ ላብ በተለይም በጭንቅላታችን ላይ ይከሰታል።
በህፃናት ላይ የሚከሰት ከልክ ያለፈ ላብም ለቫይታሚን ዲ እጥረት መጋለጣቸውን ያሳያል ተብሏል።
በጭንቅላት ላይ የሚታይ ከፍተኛ ላብ የቫይታሚን ዲ3 እጥረት ምልክት መሆኑም ተጠቁሟል።
8. ከፍተኛ የደም ግፊት
ቫይታሚን ዲ በመላ ሰውነታችን የተስተካከለ የደም ዝውውር እንዲኖር በማድረግ የልብ ጤናን ይጠብቃል።
9. ከልክ ያለፈ ውፍረት
በ2013 በለንደን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የተደረገ ጥናት ከልክ ያለፈ ውፍረት ለቫይታሚን ዲ እጥረት እንደሚያጋልጥ አመላክቷል።
ተመራማሪዎች የሰውነታችን ክብደት ከቁመታችን አንፃር (ቦዲ ኢንዴክስ) 10 በመቶ መጨመር በሰውነታችን ውስጥ የተከማቸ የቫይታሚን ዲ መጠንን በ4 በመቶ እንዲቀንስ እንደሚያደርገው አረጋግጠናል ብለዋል።

ምንጭ፦ www.top10homeremedies.com/

Advertisement