በእርግዝና ወቅት የሆርሞን ለውጥን ተከትሎ ለሚከሰተው የስኳር ህመም ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ተባለ – Hormonal Change During Pregnancy and Diabetics

                                                                     

ማህሌት ታደለ

የህክምና ተቋማትም በእርግዝና ወቅት የሚከሰተውን የስኳር ህመም መሠረት ያደረገ ክትትል ሊያደርጉ እንደሚገባ ተጠቅሷል፡፡

ትናንት የስኳር ህመም ቀንን አስመልክቶ በሸራተን አዲስ ሆቴል በተደረገ የፓናል ውይይት እናቶችም ሆኑ የጤና ተቋማት በእርግዝና ወቅት ለሚከሰተው የስኳር ህመም ትኩረት እደማይሰጡ ተነግሯል፡፡

በውይይቱ ላይ እናቶች በእርግዝና ወቅት የስኳር ህመም ሲያጋጥማቸው ምን አይነት ጥንቃቄ መውሰድ እንዳለባቸው በህክምና ባለሙያዎች ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

የኢትዮጵያ ስኳር ህሙማን ማኅበር አለም አቀፉን የስኳር ህመም ቀን አስመልክቶ ካከናወናቸው ተግባራት መካከል የትናንቱ የፓናል ውይይት አንዱ መሆኑን የማኅበሩ ፕሮግራም አስተባባሪ ወይዘሮ ምሥራቅ ታረቀኝ ነግረውናል፡፡

ምንጭ:- የሸገር FM 102.1 ሬዲዮ

 

Advertisement