ለኪንታሮት ህመም እና ለፊንጢጣ ካንሰር የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል
በቆሎ በፋየበር የበለፀገ ስለሆን እንደ ሆድ ድርቀት እና ተያይዞ የሚመጣውን የኪንታሮት ህመም ተጋላጭነት በእጅጉ ይቀንሳል።
✓ ለሰውነታችን ጠቃሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ይዟል
እንደ ፎስፈረስ ለአጥንት ጥንካሬና እድገት ጠቀሜታ ያለው እና ማግኒዚየም ለልብ እንዲሁም ለአጥንት ጥንካሬ የሚጠቅሙ ንጥረነገሮች አሉት።
✓ የኮሌስቴሮል መጠንን ይቀንሳል
በቆሎ መጥፎ የምንለውን የኮሌስቴሮል አይነት እንዲቀንስ የሚያደርግ ሲሆን ይህም ከልብ ህመም እና ሌሎች ከኮሌስቴሮል መጠን መጨመር ጋር ተያያዥነት ባላቸው በሽታዎች እንዳንጠቃ ያደርጋል።
✓ የቫይታሚን ምንጭ ነው
በቆሎ በቫይታሚን ቢ የበለፀገ ስለሆነ በተለየም ታያሚን ለነርቭ ጤናማነት ወሳኝ ሚናን ይጫወታል።
✓ የበቆሎ አንቲኦክስደንት ባህርይ ስላለው ካንሰርን የመከላከል አቅም እንዳለው ጥናቶች ያሳያሉ።
ምንጭ:- ዶክተር አለ(Doctor Alle)