የአእምሮ ጤና ከጸሀይ ብርሀን ጋር ከፍተኛ ግንኙነት አለው – ጥናት

                  

የአምሮ ጤና ከጸሀይ ብርሃን ጋር ያለው ቁርኝት ከፍተኛ እንደሆነ አንድ ጥናት አመለከተ።

የብሪግሀም ያንግ ዩንቨርሲቲ በአእምሮ ጤና ላይ በሰራው ጥናት የተላያዩ የአየር ጸባይ ሁኔታዎች ከአእመሮ ጤና ጋር ስለሚኖራቸው ተጽህኖዎች ዳሰሳ አድርጓል።

 በዚህ ጥናት በጸሀይ ብርሃንና አምሮ ጤና መካከል ያለው ግንኙነት ከሌሎች ጉዳዮች በበለጠ ተያያዥነት እንዳለው ነው የተገለጸው።

በጥናቱ የስነ አእምሮ፣ የህክምና እና የመሀበረሰብ ጤና ባለሞያዎች ተሳትፈዋል።

በጥናቱ የጸሀይ ብርሀን፣ ደመና፣ ሙቀትት፣ ዝናብና ጭጋግ በአእምሮ ጤና ላይ ሊያሳድሩት የሚችሉትን አዎንታና አሉታ ገጽታዎች አጥንተዋል ተብሏል።

በጥናቱም የጸሀይ ብርሃን አጭር በሆነባቸው ቀናት ጥናቱ በተካሄደባቸው ሰዎቹ ላይ የተስተካከለ የአእምሮ ጤና እንዳልተሰማቸው አረጋግጧል።

በዝናባማና በጭጋጋማ ቀናት ሰዎቹ የጭንቀትና የመደበት ስሜት እንደተሰማቸው የተገለጸ ሲሆን የጸሀይ ብርሃን በበቂ ሁኔታ በሚገኝበት ቀናት የሰዎቹ የመደበት ስሜት እንደቀነሰና የተሻሻለ የአእመሮ ጤና እንደተሰማቸው በጥናቱ ተጠቁሟል።

የክሊኒካል ፕሮፌሰርና የስነ ልቦና አማካሪ የሆኑት ማርክ ቢከር እንደተናገሩት በዝናባማ ወይንም በጭጋጋማ ቀን ሰወቹ ጭንቀት ወይንም የመደበት ስሜት ተሰምቷቸዋል። 

በአንፃሩ የጸሀይ ብርሃን በበቂ መጠን ሲያገኙ የመደበትም ይሁን የጭንቀት ስሜታቸው እየቀነሰ ስለሄደ የጸሀይ ብርሃን ከጉዳይ ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለው አስረድተዋል።

ቀደም ሲልም የአየር ሁኔታ በሰውች ስሜት ላይ ሊያሳድረው ስለሚችለው ሁኔታዎች የተለያዩ ጥናቶች የተካሄዱ ቢሆንም የቀድሞ ጥናቶች የተሟሉ እንዳልነበሩ ማርክ ቢከር ተናግረዋል።

ዘገባው እንደሚያስረዳው በዚህ ጥናት በርካታ ምክንያቶች የተዳሰሱ በመሆኑ ጥናቱን የተሻለ አድርጎታል ተብሏል።

የማህበረሰብ ጤና ተቋማ የሰውን አምሮ ጤና ለመጠበቅ ሰዎቹ ለረጅም ጊዜ የጸሀይ ብርሀን ማግኘት ባማይችሉበት ወቅት እግዛ ማድረግ እንዳለባቸውም ጥናቱ ያስረዳል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement