የእንቅልፍ እጥረትም ሆነ ከመጠን በላይ መሆን ከደም ግፊት፣ ከፍተኛ ከሆነ የስኳር መጠን፣ በወገብ ላይ የስብ ክምች እንዲኖር እና ጤናማ ያልሆነ ኮሌስትሮል ችግር ምክንያት ይሆናል።
አንድ ጥናት እንደሚያመለክተው ወንዶች በቀን ውስጥ ከስድስት ሰዓት በታች በሚተኙበት ወቅት ከደም ግፊት ፣ ከፍተኛ ከሆነ የስኳር መጠን ጋር ተያያዥነት ላላቸው የጤና ችግር እና በወገብ ላይ ለሚፈጠር የስብ ክምች ምክንያት ነው።
በተመሳሳይ ከስድስት ሰዓት በታች የሚተኙ ሴቶችም በወገብ ላይ ለሚፈጠር ከፍተኛ የስብ ክምችት ያላቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ እንደሆነ ጥናቱ አመልክቷል።
በዛሬ የጤና አምድ በዋነኝነት የሚቀርበው ሰዎች በቀን ውስጥ በቂ እንቅልፍ እንዳይተኙ ምክንያት ናቸው የተባሉ አስፈላጊ ያልሆኑ ልማዶች ናቸው።
የእንቅልፍ ማጣት እጥረት በአሁን ወቅት የብዙዎች ችግር እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ ሆኖም ይህ ጉዳይ ከጤና ችግር ጋር ብቻ የሚያያዝ ሳይሆን ሰዎች በህይወት ዘይቤያቸው ሊቀርፏቸው የሚገቡ አስፈላጊ ያልሆኑ የህይወት ልማዶች በመኖራቸው ነው።
ሰዎች በህይወታቸው ሊቀርፏቸው ከሚገቡ አስፈላጊ ያልሆኑ ልማዶች መካከል የሚከተሉት ናቸው።
1.በአግባቡ አለመመገብ፦
ሰዎች የሚመገቡትን ይመስላሉ የሚለው ሀረግ አብዛኛውን ሰው ለመቀበል ቢቸገርም ጉዳዩ በእንቅልፍ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንዳለው ነው የሚነገረው።
አመጋገብን በተለይ ከእንቅልፍ በፊት ያለው በሰዎች የእንቅልፍ ጥራት ላይ ተፅዕኖ ይኖረዋል።
በዚህም መሰረት ንቁ የሚያደርጉ እና ምግብ የመፍጨት ስርዓት ላይ ችግር የሚፈጥሩ ጣፋጭ እና ቅመም ያለባቸውን ምግቦችን ከእንቅልፍ በፊት ማስወገድ ይገባል ተብሏል።
ከዚህ ባለፈ ከእንቅልፍ በፊት በሰውነት ውስጥ ያለን የማላተን ሆርሞን መጨመር የሚያስችከሉ በፕሮቲን የበለፀጉ ምግቦችን መመገቡ እንደሚያስፈል ተጠቁሟል።
2. አልኮል እና ቡናን መጠቀም፦
በቡና ውስጥ የሚገኘው ካፊይን የተሰኘው ንጥረ ነገር ሰዎች ጥራት ያለው እና በቂን እንቅልፍ እንዳያገኙ የሚያደርግ ሲሆን፥ የእንቅልፍ ሰዓታቸውን ንቁ ሆነው እንዲያሳልፉ ምክንያት ይሆናል።
ይህን ችግር ለመቅረፍ ሰዎች ቡና ከማታ ይልቅ ጠዋት ላይ መጠቀም አለባቸው ተብሏል።
አልኮልን በተወሰነ መጠን መጠቀም መልካም እንደሆነ ቢነገርም መጠኑ ከፍተኛ ሲሆን፥ ሰዎች በእንቅልፍ ሰዓት ለተለያዩ ጉዳዮች እንዲነቁ ምክንያት በመሆን የእንቅልፍ ሰዓታቸውን ያዛባባቸዋል።
3. ምቾት በሌለው የመኝታ ክፍል መታኛት፦
የሰዎች የመተኛ ክፍል በእንቅልፍ ጥራትና በቂ መሆን ላይ ከፍተኛ የሆነ ተፅዕኖ እና አስተዋፅኦ አለው ተብሎ ይታመናል።
የተሻለና ጥራት ያለው እንቅልፍን ለማግኘት ሰዎች የመኝታ ቤታቸውን በአዲስ መልኩ በመቀየር መልካም የእንቅልፍ ጊዜ እንዲኖቻው ማድረግ ይችላሉ።
ከዚህ ውጭ በመኝታ ክፍል ውስጥ ያለን ብርሃን መቀነስ ያስፈልጋል። እንደ ባለሙያዎች ገለፃ ሚላተን የተሰኘው ለእንቅልፍ አስፈላጊ የሆነ ንጥረ ነገር በብርሃን ምክንያት ተፅዕኖ የሚደርስበት በመሆኑ በመኝታ ቤት ብርሃን መቀነስ ያስፈልጋል።
4. ስልክን አብዝቶ መጠቀም፦
የስልክ እና የሌሎች ስክሪኖች የሚለቋቸው ብርሃኖች አዕምሮን ንቁ በማድረግ እንቅልፍን እንደሚከለክሉ ነው የሚነገረው።
ከዚህ ባለፈ ሰዎች ስልካቸውን በሚጠቀሙበት ወቅት ከሚደርሳቸው መልዕክቶች እና በተለያዩ ምክንታቶች ለጭንቀት እና ውጥረት የሚያጋለጡ በመሆኑ ወደ መኝታ ከመሄዳቸው በፊት ከስልክ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ማጠናቀቅ አለባቸው ተብሏል።
5. ከፍተኛ የፍርሃት ስሜት፦
ሰዎች ከስራ፣ ገንዘብ፣ ጤና እና በተለያዩ ምክንያቶች አዕምሮቸው በፍርሃትና ስጋት ውስጥ ያልፋሉ።
ይህም የስጋትና ፍርሃት ስሜት ሰዎች አስፈላጊ የሆነውን እንቅልፍ እንዳያገኙ የሚያደርግ መሆኑ ተጠቁሟል።
6. ሰውነትን ዘና አለማድረግ፦
እንቅልፍ በተገቢ ሁኔታ ለማግኘት የሚያልፍባቸው የራሱ ደራጃዎች አሉት። ከዚህ ውሰጥም እራስ ዘና ማድረግ ይገኝበታል።
በመሆነም እራስን ዘና ለማድረግ ተመስጦ፣ የአካል እንቅስቃሴ እና በተወሰነ መልኩ ከእንቅልፍ በፊት ሻወር መውሰድ ልምድ ማድረግ እንደሚገባ ተነግሯል።
ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)
The colon after each year is not had. cheap sildenafil online Kfcmny qocfgv
cdb oils http://cbdhempoilwr.com/# – cbd hemp cbd for dogs cbd hemp
cbd capsules cbd drops pure cbd oil