አፋችን ውስጥ ቁስል፣ ውሃ መቋጠርና፣ ቀይ መሆን ሊከሰት ይችላል፡፡ ይህ ቁስለት በጉንጭ የውስጠኛው ክፍል እንዲሁም በምላስና በከንፈር አካባቢ ተደጋግሞ ሊፈጠር ይችላል፡፡የዚህ አይነቱ ችግር ሁሉንም ሰው ሲያጋጥም ይስተዋላል፡፡ የዚህ ችግር መነሻ ከሚባሉት መካከል የምግብ አለመስማማት፣ የሆርሞን መለዋወጥ፣ ድርቀት፣ ጭንቀት፣ የቫይታሚን B እና C እጥረት ይጠቀሳሉ፡፡ ህመሙ ከተከሰተ እስከ 10 ቀናትና ከዚያ በላይ ሊቆይ እንደሚችል የጤና ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡ የዚህ አይነቱን የአፍ ውስጥ ችግር በምን መልኩ በቤት ውስጥ ማከም እንችላለን?
1. አንድ የሾርባ ማንኪያ ማር እና አንድ ማንኪያ የኮኮናት ወተትን መደባለቅና ችግሩ ባለበት አካባቢ በቀን 3 ጊዜ መቀባት፡፡
2. አንድ የሻይ ማንኪያ ደቃቅ ጨውን በአንድ ብርጭቆ ውሃ በመደባለቅ መጉመጥመጥ፡፡ ቤኪንግ ሶዳን እንደ አማራጭ መጠቀምም ይቻላል፡፡
3. ከነዚህ አማራጮች ውጪ ሌላ ካስፈለገንም ማርን በአፋችን ውስጥ በማድረግ የተወሰነ ደቂቃን ሳንውጠው ማቆየት ጤናማ እንድንሆን ያስችለናል፡፡
ምንጭ:- ዶክተር አለ (Doctor Alle)