መግባባት ያለበት ጽኑ ፍቅርና መተማመን ላይ የተመሰረተ ግንኙነትን መገንባት ረዘም ላለ የአብሮነት ቆይታ እና ለትዳር አጋዥ መሆኑን የስነ ልቦና ባለሙያዎች ይናገራሉ።
ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ ማስመሰል፣ መዋሸት እና ማታለል ለፍቅር ጊዜ ማጠር ምክንያት እንደሚሆንም ነው የሚናገሩት።
ባለሙያዎቹ ለፍቅር እድሜ ማጠር ምክንያት ያሏቸውን ሶስት መጥፎ ልማዶችም ይጠቅሳሉ።
ሃላፊነትን በተደጋጋሚ ለማስታወስ መሞከር፦ አንደኛው አጋር ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ሲዘረዝርና ለችግሮቹ መፍትሄ ማበጀትን ሲያውጠነጥን ከዚህ በተቃራኒው መጓዝ እንደማይገባ ባለሙያዎች ይገልጻሉ።
ከዚህ ጋር ተያይዞ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ሌሎች ነገሮች እያሉ፥ ጥቃቅን የሆኑ ሃላፊነቶችን ተወጣህ/ ተወጣሽ በማለት አስታዋሽ መምሰሉ አላስፈላጊ እንደሆነም ያስረዳሉ።
የመመገቢያ ሳህኖችን እንዳጠበ እና እንዳጠበች፣ መከፈል የሚገባቸው ነገሮች ካሉም ያንኑ አድርገሃል ወይ ብሎ መጠየቅና ሃላፊነት መስለው የሚታዩንን ነገሮች እንደተወጣ አሁንም አሁንም መደጋገም አላስፈላጊ ይሆናል ነው የሚሉት።
ምክንያቱም መሰል ጣልቃ ገብነቶች ያንን ግለሰብ ስራውን እንዳልተወጣና እንዳልከወነ ማሳያዎች ይሆናሉና በጊዜ ብዛት መለያየትን ያስከትላሉ።
ከዚያ ይልቅ ግን የፍቅር ወይም የትዳር አጋርዎ የራሱን ድርሻ መወጣት የሚችልበትን መንገድ ቤት ውስጥ ማመቻቸትና ያንኑ ለባለጉዳዩ መተውን ልመዱ ሲሉም ይመክራሉ።
በተንቀሳቃሽ ስልክ የጽሁፍ መልዕክት መለዋወጥ፦ ስልክ አይደወል ባይባልም ከፍቅረኛዎ ወይም ከትዳር አጋርዎ ጋር አብረው በሆኑ ጊዜ በዕሁፍ መልዕክት መላላክ አግባብ አይደለም።
አጋርዎ አብሮዎት እያለ ስልክ ሲደወል በተቻለ መጠን ምላሽዎን በንግግር ማድረግን ይልመዱ።
ይህ ሳይሆን ቀርቶ ግን ምላሽዎት በጽሁፍ መልዕክት ከሆነ አብሮዎት ላለው ሰው ክብር አለማሳየት መሆኑን ነው ባለሙያዎቹ የሚገልጹት።
መልዕክቱም አጋርዎን አታስፈልገኝም እንደማለት ነውና ከዚህ ድርጊት ይቆጠቡ።
ከዚያ ይልቅ አብሮዎት ላለው ሰው ፍቅርና መውደድዎን በማሳየት የጽሁፍ መልዕክቱንም ሆነ ስልክ ላይ ጊዜ ማጥፋቱን ለሌላ ጊዜ ይተውት።
ሙሉ ትኩረትዎን እርሱ ላይ በማድረግ ግንኙነትዎን ማሳደግና ማጠናከርም ይችላሉ።
አንዳንድ ነገሮችን አብሮ መከወን መጨዋወትና ሃሳብ መለዋወጥም መልካም ነውና ያንኑ ማዳበር።
የጋራ ጊዜ አለመኖር፦ በህይዎትዎ ምንም ያክል ሃላፊነት ቢኖርብዎትም የተወሰነ ጊዜ ለፍቅር አጋርዎ መስጠትና ከቤት ወጣ ብሎ በመዝናናት ስሜት መጨዋወት የፍቅር ቅመም እንደሆነ ይነገራል።
ታዲያ ከዚህ በተቃራኒው ሆነው ምንም ባያጎድሉም የራስ የሆነ ጊዜ ሳይኖር አብሮ ማሳለፉ ተቃራኒ ውጤት አለው።
አብረው እየተዝናኑ በመጨዋወት ማሳለፍ እና መሳሳቅ ለሁለቱም መልካም የፍቅር ጊዜ ትዝታን ያጭራል።
ከዚህ አንጻርም ይህን ማድረጉ ለፍቅር ባላ ይሆናልና እንደዛ ማድረጉን ማዳበር መልካም መሆኑን ባለሙያዎች ይገልጻሉ።
በተቃራኒው ምንም ባይጎድል እንኳን ቤት ውስጥ በመቀመጥ ብቻ ማሳለፉ መሰለቻቸትን ያመጣልና ጊዜን አብሮ ማሳለፍ ምርጫችሁ አድርጉ።
ወጣ ብሎ የእግር ሽርሽር ማድረግ፣ ሲኒማ ገብቶ ፊልም መመልከት፣ ሻይ ቡና ማለት፣ ሙዚቃ እያደመጡ በመጨዋወትና በመሳሰሉት የአብሮነት ጊዜን ማሳለፍ ይቻላል።
አለማዳመጥ፣ ከመነጋገር ይልቅ በይሆናል መመራትና መወሰን፣ የራስን ሃሳብ በእነርሱ ላይ ለመጫን መሞከር እና ነገሮችን ከማስረዳት ይልቅ መተቸትም ለፍቅር ግንኙነት መቋረጥ የሚዳርጉ ልማዶች ናቸውና ያስወግዷቸው።
ምንጭ፦ psychology today