የአመጋገብ ችግር (Eating disorder)

ለአመጋገብና ለሰውነት አቋም ያለን አመለካከት እጅግ በጨመረበት ዘመናዊው አለም በተለይም በዝነኛ ሰዎች ላይ ጎልቶ የሚታየው የአመጋገብ ችግር (Eating disorder) ከጊዜ ወደ ጊዜ ብዙ ወጣትና ጎልማሶች ላይ መታየት ጀምሯል፡፡ ችግሩ በወንዶችም ሆነ በሴቶች ላይ የሚከሰት ሲሆን በብዛት የሚስተዋለው ግን ሴቶች ላይ ነው፡፡ የስነልቦና ባለሞያዎች የአመጋገብ ችግርን (Eating disorder) በሶስት ይከፍሉታል፡፡

ራሰን የማስራብ ችግር (Anorexia Nervosa)

  • በዚህ ችግር የተያዙ ሰዎች የራስ መተማመናቸው በከፍተኛ ሁኔታ ከአካላዊ ገፅታቸው ጋር የተቆራኘ ነው፡፡
  • በቀን ውስጥ በጣም ትንሽ ምግብ በመመገብ ሰውነታቸው በቂ ንጥረነገር እንዳያገኝ ያደርጋሉ፡፡
  • ክብደት አጨማራለው የምል ከፍተኛ ፍርሀትና የተደጋገመ ሀሳብ (obsession) አለባቸው፡፡
  • ሰውነታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየመነመነ አጥንታቸው ቢወጣ አንኳን እራሳቸውን አንደ ወፍራም ስለሚመለከቱ ራስን የማስራብ ልምዳቸውን አያቋርጡም፡፡

እየበሉ የማስወጣት ችግር (Bulimia Nervosa)

  • በዚህ ችግር የተያዙ ሰዎች ብዙ ምግብ ያለአግባብ የሚመገቡ ሲሆን ከተመገቡ በኋላ ግን የበሉትን ሙሉ ለሙሉ ያስወጡታል፡፡
  • ስለውፍረት መቀነስ ከሚገባው በላይ የሚጨነቁ ሲሆን ስለችግራቸው ግን የግትርነት አቋም አላቸው፡፡
  • ከሰዎች ለሚሰጣቸው አስተየየት ትልቅ ግምት የሚሰጡና በራስ መተማመናቸው ዝቅ ያለ ነው፡፡
  • በጣም የመክሳትና የመጠውለግ ነገር ቶሎ ስለማያሳዪ እርዳታ ሳያገኙና ችግራቸው ሳይታወቅ ለረጅም ጊዜ ይቆያሉ፡፡
  • ይህ ችግር በታዋቂ ሰዎች ላይ የሚጎላ ሲሆን ልእልት ዲያና፣ ኦፕራና ቪክቶሪያ ቤካም ከብዙ የችግሩ ተጠቂዎች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

ከልክ በላይ የመመገብ ችግር (Binge eating disorder)

  • ብዙ የመመገብ ሱስ ሲሆን በዚህ ችግር የተያዙ ሰዎች ላለመወፈር ወይም አላስፈላጊ የስብ ክምችታቸውን ለማቃጠል የሚያደርጉት ምንም አይነት ጥረት የለም፡፡
  • ከልክ በላይ በመመገባቸው ምክንያት የወንጀለኝነትና የእፍረት ስሜት ስላለባቸው ለብቻቸው መመገብን ያዘወትራሉ፡፡
  • ሳይርባቸውና ምግብ ሳያስፈልጋቸው የሚመገቡ ሲሆን ከልክ በላይ/ቁንጣን አስኪይዛቸው መመገብን ልማደቸው ያደርጋሉ፡፡

የአመጋገብ ችግሮች መንስኤ ምንድ ነው?

የአመጋገብ ችግሮች ውስብስብ ችግሮች ናቸው ምንም እንኳን የአመጋገብ ችግሮች ትክክለኛ መንስኤ ባይታወቅም ባጠቃላይ የስነ-ህይወት ፣ የስነ-ልቦና እና / ወይም የአካባቢ አካባቢያዊ ጥምረት ለእነዚህ በሽታዎች እድገት አስተዋጽኦ ያበረክታል።

የባዮሎጂካዊ ምክንያቶች ምሳሌዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ: –

  • መደበኛ ያልሆነ የሆርሞን ተግባራት
  • የጄኔቲክስ (በአመጋገብ ችግሮች እና በአንዱ ጂኖች መካከል ያለው ትስስር አሁንም በጥልቀት ጥናት እየተደረገ ነው ፣ ነገር ግን የጄኔቲክስ የታሪኩ አካል እንደሆነ እናውቃለን)።
  • የምግብ እጥረት

የስነልቦና ምክንያቶች ምሳሌዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ: –

  • አሉታዊ የአካል ምስል
  • ደካማ በራስ መተማመን

ምንጭ: ዶክተር አለ

Advertisement