የቀይ የደም ህዋስ መጨመር (Polycythemia)

ቀይ የደም ህዋስ መጨመር ማለት ትክክለኛ ከሆነ በደም ስሮች ውስጥ ቀይ የደም ህዋስ ማሰራጨት በተለያየ ምክንያት እንዲጨምር ሲያደርግ ነው አንዳንድ ጊዜ ይህ በሚጨምርበት ጊዜ ተያይዞ ሄሞግሎቢን እና ሄናቶክራይት እንዲጨምር ያደርገዋል።

የቀይ የደም ህዋስ ለምን ይጨምራል?

 • የመጀመሪያ ደረጃ የቀይ የደም ህዋስ መጨመር – ይህ ብዙውን ጊዜ ምክንያቱ የማይታወቅ ሲሆን ተፈጥሮ ወይም በማይታወቅበት ሁኔታ በቀይ የደም ህዋስ ምርት ሂደት ውስጥ ችግር ሲኖር ነው።
 • በሁለት አይነት ምክንያት የሚጨምር ሲሆን እነሱም

ሁለተኛ ደረጃ የቀይ የደም ህዋስ መጨመር – ይህ የሚከሰተው በሌላ ህመሞች ምክንያት ወይም ውስጣዊ ችግር ምክንያትየሚከሰት ነው።

ምክንያቶቹ

 • ዝቅተኛ የደም ኦክስጅን መጠን መኖር
 • እጢ ካለ
 • የልብ ህመም
 • የሳንባ በሽታዎች
 • የደም ግፊት
 • ሲጋራ ማጨስ
 • የአጥንት በሽታ
 • አንዳንድ መድሃኒቶች

የቀይ የደም ህዋስ ሲጨምር የምናየው ምልክቶች

 • ድካም ፣ትኩረት ማጣት
 • ትንፋሽ ማጠር
 • ራስ ምታት
 • የእቅልፍ እጦት
 • የመገጣጠሚያ ህመም
 • የሰውነት ከመጠን በላይ ማላብ
 • የድድ መድማት እና በቀላሉ መድማት
 • የደረት ህመም፣ የእጅ እና የእግር መሞቅ
 • የእይታ መደብዘዝ፣ የጆሮ መጮህ

መፍትሄው

 • የሄሞግሎቢን እና የሄማቶክሪት መጨመር ካለ ደማቸው ተቀድቶ እንዲቀንስ ያደርጋል
 • ሲጋራ ከማጨስ መቆጠብ
 • እንዳመጣው ሁኔታ ወይም እንደምክንያቱ መፍትሄውም ስለሚለያይ በመጀመሪያ እነዚህን መለየት እና ማከም ያስፈልጋል

ስለዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን ምልክቶች ካዩ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ህክምና ያድርጉ።

ምንጭ: ዶክተር አለ

Advertisement