የማስታወስ ችሎታን በ75% የሚጨምረው ቅጠል

በሀገራችን በተለይ በገጠራማው ክፍል የስጋ መጥበሻ ወይም ሮዝሜሪ በመባል የሚጠራው ቅጠል በየጓሮው እናስተውላለን፤ ነገር ግን ጠቀሜታው ጊቢ ከማሳመርና አልፎ አልፎ ስጋ ሲጠበስ እንደማጣፈጫነት ከመጠቀም በዘለለ እንብዛም አይታወቅም፡፡

ሮዝሜሪ ወይም የጥብስ ቅጠል ምንድን ነው?

ሮዝሜሪ ለጤና ብዙ ጠቀሜታ አለው፡፡ ጥናታቸውን ሮዝሜሪ ላይ ያደረጉ ባለሙያዎች በቅርቡ ባወጡት መረጃ የማስታወስ ችሎታን 75 ከመቶ ከፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ይህ ተክል ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎችም አሉት፡፡ ሮዝሜሪ ለምግብ ማጣፈጫነትም በስፋት ጥቅም ላይ ይዉላል፡፡ በአብዛኛዉም ለስጋ ጥብስ ጥሩ መአዛ እና ጠአምን ስለሚሰጥ ለስጋ መጥበሻነት ያገለግላል። የጥብስ ቅጠል የሚለዉን ስያሜም ያገኘዉ ከዚሁ አገልግሎቱ የተነሳ ነዉ። የሮዝሜሪን የዘይት ፋብሪካዎችም ዘይት ለማምረት በጥሬ እቃነት ይጠቀሙታል፡፡

የሮዝሜሪ ተክል የማስታወስ ችሎታን የማሳደግ ሚስጥር አዲስ ግኝት አይደለም። የዚህን ተክል የማስታወስ ችሎታን ማሰደግ በጥንት ዘመን ስነጽሁፎች ዉስጥ ሳይቀር ተገልጾ ይገኛል፡፡ ስለዚህ ተክል በዊልያም ሼክስፔር ሀምሌት መጽሀፍ ላይ ተጽፎ እናነባለን፡፡ በጥንት ጊዜ በጋብቻ ስነስርአት ላይ እንደ መታሰቢያ መልክት ሆኖ ያገለግል ነበር፡፡ በተጨማሪም በአውሮፓ እና በአውስትራሊያ የጦርነት መታሰቢያ ምልከት አድርገው ይጠቀሙበት ነበር፡፡

ሀዘንተኞችም ባለቁልፍ ልብስ በመልበስ፤ እጣን በማጨስ እና ሮዝሜሪ ወደ ᎂች መቃብር በመወርወር መታሰቢያ ስርአት ያደርጉ ነበር፡፡ ይህ የሮዝሜሪ ተክል በርግጥ የቆየ እና የጥንት ባህል ቢሆንም መነሻው ግን በመካከለኛው ዘመን ከአረቡ አለም ወደ ሳይንሳዊ እሳቤነት እንዳደገ ይገመታል፡፡ የተለያዩ ሳይንቲስቶች ባጠኑት ጥናት ሮዝሜሪ የማስታወስ ችሎታን ለማሳደግ ጠቃሚ እንደሆነ ነው፡፡

በ2012 ዓ.ም በአማካኝ 75 አመት እድሜ ያስቆጠሩ ሰዎች ላይ በተደረገ ጥናት የደረቀ የሮዝሜሪ ቅጠል ዱቄት እንዲጠቀሙ በማድረግ የሚያስደንቅ ውጤት ተገኝታል፡፡ በዚሁ ጥናት ላይ የሮዝሜሪ ዘይት የማስታወስ አቅምን በሚያስደንቅ ሁኔታ እስከ 75 በመቶ የማሳደግ አቅም እንዳለው ተረጋግጧል፡፡

ሌሎች የጥብስ ቅጠል የጤና ጥቅሞች

  • የአፍ ጠረንን ለማስወገድ
  • የቆዳ መሸብሸብን ይከላከላል
  • ካንሰርን ይከላከላል
  • የማይግሬን ህመምን ያስታግሳል
  • የፀረ ባክቴሪያነት ጥቅም
  • በሽታን የመከላከል አቅምን ያዳብራል

ምንጭ: ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement

2 Comments

Comments are closed.