አዲስ የተወለዱ ህፃናት ላይ ኢንፌክሽን ሲኖር የምናስተውላቸው ምልክቶች

ህፃናት ላይ ኢንፌክሽን ሲኖር ልናስተውላቸው ምልክቶች በአብዛኛው አደገኛ ከሚባሉት ውስጥ የሚካተቱ ናቸው፡፡እነሱም፡-

  1. ኢንፌክሽን ሊያስከትሉ የሚችሉ ሁኔታዎች፦
  • እትብቱ ሳይደርቅ በሳሙና ማጠብ
  • እትብቱ ሳይደርቅ በእጅ መነካካት ካለ
  • ለባክቴሪያ ተጋላጭ ከሆኑ
  • በጡጦ የምናጠባቸው ከሆነ
  • ቫይረስ
  • በወሊድ ጊዜ የእናትየው ማህፀን በባክቴሪያ የተጠቃ ከሆነ

2. አደገኛ ምልክቶች

  • ፈጣን አተነፋፈስ፦ ሲተኙ ወይንም ሲያርፉ በደቂቃ ከ60 በላይ ከተነፈሱ
  • አየር ለማግኘት መታገል፦ ሕፃን ሲተኛ ወይንም ሲያርፍ ደረት ወደውስጥ መሳብ፣ አየር ለመሳብ የጥረት ድምጽ ሲሰማ፣ የአየር መውሰድ ጥረት አፍንጫን ሲገፋ ደረት ወደውስጥ መሳብ አፍንጫ ትንፋሽ ሲገፋ
  • ትኩሳት፡- ከ37.5º ሴንቲግሬድ በላይ ወይንም በጣም ሲቀዘቅዙ ከ35.5ºሴንቲግሬድ በታች
  • ሀይለኛ መንደብደብ፡- ከብዙ ብጉር ጋር ወይንም የቆዳ መነፋፋት (ትንንሽ መንደብደብ የተለመደ ነው)
  • አለመመገብ
  • አልፎ አልፎ ብቻ ከእንቅልፍ መነሳት እና ምንም መልስ ከሕፃን አለማየት ለምታረጉት ነገሮች

መንቀጥቀጥ፦እራስ መሳት ወይንም የመፈራገጥ ንቅናቄ

3. መፍተሄው

ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶችን ሲያስተውሉ ወደ ህክመና ተቋም በመውሰድ አስፈላጊውን ህክምና እንዲያገኙ ማድረግ ይገባል፡፡

ምንጭ: ዶክተር አለ (Doctor Alle)

Advertisement

14 Comments

  1. I love looking through a post that can make people think. Also, many thanks for permitting me to comment!

Comments are closed.