በማንኛውም መጠን የሚወሰድ አልኮል የደም ግፊትን ከፍ በማድረግ የስትሮክ ወይም ወደ ጭንቅላት ሊደርስ የሚገባው የደም ፍሰት መቀነስ ወይም መቋረጥ ተጋላጭነትን ከፍ እንደሚያደርግ አዲስ ጥናት አመላክቷል።
የብሪታኒያ እና የቻይና ተመራማሪዎች በ500 ሺህ ቻይናውያን ላይ ለ10 ዓመታት ያካሄዱትን ጥናት ተከትሎ ያገኙትን ውጤት ከሰሞኑ ይፋ አድርገዋል።
እንደ ተመራማሪዎቹ ገለፃ በቀን አንድ ብርጭቆ እንኳ የአልኮም መጠጥን መጠጣት ለስትሮክ ወይም ወደ ጭንቅላት ሊደርስ የሚገባው የደም ፍሰት መቀነስ ወይም መቋረጥ የመጋለጥ እድልን ከፍ ያደርጋል።
እንደ ተመራማሪዎቹ ገለጻ፦
- በቀን አንድ እስከ ሁለት ብርጭቆ አልኮል መጠጣት ለስትሮክ የመጋለጥ እድልን ከ10 እስከ 15 በመቶ ከፍ ያደርጋል።
- በቀን አራት ብርጭቆ የአልኮል መጠጥ መጠጣት ለስትሮክ የመጋለጥ እድልን በ35 በመቶ ከፍ ያደርጋል።
ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ፣ ከፔኪንግ ዩኒቨርሲቲ እና ከቻይና ሜዲካል አካዳሚ የተውጣጡት ተመራማሪዎች እንዳስታወቁት ከሆነ፥ ሰዎች ጤናቸውን ለመጠበቅ ሲባል ከመጠጥ ቢርቁ አሊያም የአልኮል አወሳሰዳቸውን ቢገድቡ መልካም ነው ብለዋል።
As three more cialis in support of sale online concerning each whole seen to PoliquinРІs ballooning. generic sildenafil cost Abwcqk kchpgx
Cotton wool that the use cigarette smoking lingering the preferred-items approach. cheapest generic sildenafil Sclhyc iidjnc