የእውነተኛ ስሜት መጥፋት

የሳይኮሲስ ችግር የሚታይበት ሰው አጠቃላይ ችግሮቹ በግላዊ ፤ በማህበራዊና በሥራ ላይ ተፅኖ ሲፈጥሩበት ይታያሉ።
የሳይኮሲስ ክስተት የደረሰበት ሰው ከተጨበጠው እውነታና የፀባይ ለውጥ እንደሚደርስበት ፍንጭ ይሰጣል።
የሳይኮሲስ ምልክት የሚታይባቸው ሰዎች ግን እውነተኛው ስሜታቸው ስለጠፋባቸው የሳይኮሲስ ክስተቶቹ በራሳቸው እንዳሉባቸው ማወቅ አይችሉም።

ምልክቶቹ ምን ምን ናቸው?

የበሽታው ምልክቶች ከሰው ሰው ይለያያሉ፡፡
የሳይኮሲስ ቅድመ ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታል
• የእንቅልፍ ሁኔታ ይለወጣል። 
• የመብላት ፍላጎት ይለወጣል። 
• እራስን ከማህበራዊ ግንኙነቶች ማግለል። 
• እራስን አለመንከባከብና ንጽሕናን በሚገባ ያለመጠበቅ። 
• ከሌላ ሰው ጋር በአግባቡ አለመነጋገር። 
•በሃሳቦችና በድርጊቶች ላይ ግትር መሆን።ህመሙ የበረታበት ሰው የሚከተሉትን ምልክቶች ያሳያል

1.የቁም ቅዠት 
• የሌለውን ነገር ለምሳሌ የማይታዩ ነገሮችን ማየት
• ሌላ ሰው የማይሰማውን መስማት፣ 
• (ሰሜት) – መቅመስ ወይም ማሽተት፤
ግለሰቡ በጭንቅላቱ ውስጥ ድምፅ ሊሰማ ይችላል ወይም የሌለን ነገር ሊያይና ስሜቱን ሲያገኝ ፤ አንዳች ነገር በቆዳው ስር እንደሄደ ሲያስብ የመሳሰሉት የቁም ቅዠቶች በጣም ያስጨንቁታል። 
የቁም ቅዠት የደረሰበት ሰው ጠበኛና ለማነጋገር አስቸጋሪ ነው።

2. እራስን ታላቅ አድርጎ ማየት 
ለምሳሌ ግለስቦቹ እንደ ሲኒማ ተዋናይ ወይም መንፈሳዊ መሪ በጣም ታዋቂ ነኝ ብለው ያስባሉ። 
አንዳንድ ዘፈኖች በነሱ ላይ ያተኮረ ድብቅ መልእክት አላቸው ወይም የተለየ ሃይል አለኝ ብለው ያምናሉ።

3. ተጠራጣሪነት 
ለምሳሌ ግለሰቡ በማይታዩ ሃይሎች ወይም በሌሎች ሰዎች ክትትል፤ ሴራ ወይም ቁጥጥር እየተደረገባቸው እንደሆነ ያስባሉ። 
እየተሳደዱ መሆናቸውን ያለአንዳች ምክንያት እንኳ ያምናሉ ወይም ይጠራጠራሉ።

4. የአነጋገር ወይም ፀባይ መዘበራረቅ 
ለምሳሌ ግለሰቦቹ ፈጠን ፈጠን እያሉ ሊያወሩ ይችላሉ፤ ከአንድ አርዕስት ዘለው ወደ ሌላ ርዕስ ቶሎ ቶሎ 
ይቀይራሉ ወይም እራሳቸውን መግለጥ ይቸገራሉ የቀንበቀን ሥራ ማለትም እንደ ምግብ ማብሰልና ማፅዳት አይነት ስራዎች ያዳግታቸዋል ወይም በሁኔታዎች ላይ ተገቢውን ምላሽ አይሰጡም።

5. የስሜት ለውጥ 
ለምሳሌ፤ ለሚገጥሟቸው የሁኔታ ለውጦች ግለሰቦቹ ተገቢውን ስሜት አያሳዩም ወይም ብዙ አይናገሩም።

6. መሸበር 
ለምሳሌ ግለሰቡ ፍርሃት በጣም ሊሰማው ይችላል ወይም ይጨነቅና መረጋጋት ያቅተዋል።
– እነዚህ ምልክቶች ለሰዓታት ወይም ለቀናት ሊቆዩ ይችላሉ ።
– ግለሰቡ ተገቢውን ህክምና ካላገኘ፤ ከዚያም አልፎ ለብዙ ሳምንታት፤ ወራት ወይም ዓመታትም ሊቆይበት ይችላል።

ምንጭ: ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.