የሸንኮራ ጭማቂ የጤና ገጸ-በረከቶች

• በውስጡ ባለው ሽንትን የማሸናት ባህሪይ ከሽንት ቧንቧ ኢንፊክሽን እና ከ ኩላሊት ጠጠር ይከላከላል፣ ብሎም ኩላሊት ስራዋን በትክክል እንድታከናውን ይረዳል።

• የሸንኮራ ጭማቂ በ ካርቦሀይድሬት፣ በፕሮቲን፣ በአይረን፣ በ ፖታሲየም እና በሌሎች ንጥረ ነገሮች የበለጸገ ስለሆነ በበጋ ወቅት ተመራጭ መጠጥ ያደርገዋል።

• በውስጡ በያዘው ሰገራን የማለስለስ ባህሪይ የሆድ ድርቀትን ይከላከላል፣ የአንጀት እንቅስቃሴንም ይጨምራል።

• ባለው አልካላይን ባህሪይ በአሲድ ምክኒያት የሚፈጠርን የጨጓራ ህመም ይቀንሳል።

• የስኳር መጠኑም አንስተኛ ስለሆነ ሳይበዛ ለስኳር ህመምተኞችም ይመከራል።

• የሸንኮራ ጭማቂ በያዛቸው የካልሲየም እና የፎስፈረስ ማዕድኖች የጥርስ መቦርቦርን እና መጥፎ የአፍ ጠረንን ይከላከላል።

• በውስጡ ባለው ፀረ መርዛማነት ባህሪው የተለያዩ ኢንፌክሽኖችን ይዋጋል፣ ብሎም የበሽታ መከላከል አቅማችንን ያጎልብታል።

ምንጭ: ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement

4 Comments

Comments are closed.