በቂ እንቅልፍ በሽታ የመከላከል አቅምን ለማሻሻል ያለው አስተዋፅዖ

የተለያዩ የጥናት ውጤቶች በተደጋጋሚ በቂ እንቅልፍ ለአካላዊ እና አዕምሮአዊ ጤና አስፈላጊ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡

የጀርመኑ ቱቢንጌን ዩኒቨርስቲ የጥናት ቡድን በቂ እንቅልፍና በሽታ የመከላከል ስርዓትያላቸውን ግንኙነት በተመለከተ ጥናት አካሄዷል፡፡

ይህ ጥናት በቂ እንቅልፍ በሽታ የመከላከል ስርዓትን እንደሚያሻሽል አስታውቋል፡፡

ጥራት ያለው እንቅልፍ ማግኘት ለጤና እና በውሏችን ንቁ ሆኖ ለመዋል ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው በጥናታቸው አመልክተዋል፡፡

በቂ እንቅልፍ አለማግኘት የበሽታ ተጋለጭነትን እንደሚጨምር ጥናቱ ያመለከተ ሲሆን፥ ለልብ እና የደም ቧንቧ ተጋላጭነት ምክንያት መሆኑ ተመልክቷል፡፡

በቂና ጥራት ያለው እንቅልፍ ቲ ሴል የተሰኘውን በሸታ የመከላከል ስራዓት ውጤታማ እንዲሆን ያስችሏል ተብሏል፡፡

ቲ ሴል ጉዳት ሊያስከትል የሚችል ውጫዊ አካል ወደ ስርዓቱ በሚገባበት ወቅት በሽታን ለመከላከል ምላሽ የሚሰጥ ነው ተብሏል፡፡

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

4 Comments

Comments are closed.