ነስርን እንዴት መከላከል ይቻላል?

በአፍንጫ ላይ በርከት ያሉ የደም ስሮች የሚገኙ በመሆኑና በተፈጥሯዊ አቀማመጣቸው ምክንያት በቀላሉ ለጉዳት ስለሚጋለጡ የአፍንጫ መድማት (ነስር) በቀላሉ ሊከሰት እንደሚችል ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡

የአፍንጫ መድማት በአየር ድርቀት፣ በአፍንጫ መቁሰል፣ በቅዝቃዜ፣ በጉዳት እና በሌሎች ምክንያት ሊከሰት ይችላል።

ባለሙያዎችም ነስርን መከላከል የሚቻልባቸው መንገዶችን ይጠቁማሉ፤

ህፃናት በጣቶቻቸው አፍንጫዎቻቸውን በመንካት እንዳይልጡ መጠበቅ፤

ሞቃት አየር በሚኖርበት ወቅት ርጥበት የሚፈጥር ነገር መጠቀም፤

ሲጃራ አለማጨስ፡- ሲጋራ ማጨስ አፍንጫን እንደሚያደርቅና እንደሚያስቆጣ ጥናቶች ያመላክታሉ፤

በሚያነጥሱበት ወቅት አፍዎን መክፈት ነስርን መከላከልና ለማስቆም መፍትሄ መሆኑንም ባለሙያዎች ይናገሉ፤

ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ ውጥረትና መጨናነቅን በመቀነስ ራስን ዘና ማድረግ፣ ነስር ሲያጋጥም አለመቀመጥ እና አለመንጎንበስ ችግሩን ለመከላከል ከሚያስችሉ ዘዴዎች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement