እርግዝና ምንድን ነው?

በእርግዝና ወቅት የሚደረግ የነፍሰጡር እናት የህክምና ክትትል እና እንክብካቤ የእናትየውንና የሚወለደውን ህፃን ጤና ለመከታተልና የተሻለ ለማድረግ ከማስቻሉም በላይ ከእርግዝና ጋር የተያያዙ የጤና ችግሮች እንዳይከሰቱ ና እንዲቀንሱ ይረዳል፡፡

የእርግዝና ምልክቶች

-የወር አበባ መቅረት 
-የጡት መደደር 
-ማቅለሽ 
-ድካም መሰማት 
-የሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት 
-የራስ ምታት

በእርግዝና ወቅት ሊከሰቱ የሚችሉና ልዩ ጥንቃቄ ሊደረግባቸው የሚገባቸው ነገሮች፡- 
-ከማህፀን የሚወጣ ደም ወይም ሌላ ፈሳሽ መኖር

-የፊት፤የእጅ እና የእግር ማበጥ 
-ረጅም ግዜ የሚቆይ ራስ ምታት 
-የአይን ብዥ ማለት 
-የማይታገስ የሆድ ህመም እና የጀርባ ህመም 
-የማያቋርጥ ማስመለስ 
-ትኩሳትና ብርድ ብረድ ማለት 
-የፅንስ እንቅስቃሴ ከወትሮው መቀነስ 
-ሽንት ሲሸኑ ማቃጠል እና የሽንት መጠን መቀነስ

ምንጭ: ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement

3 Comments

Comments are closed.