ጎግል የሰዎችን ማንነት በፊት ገጽታ መለየት የሚያስችለውን ቴክኖሎጅ ለገበያ እንደማያቀርብ ገለፀ

ጎግል የሰዎችን ማንነት በፊታቸው ገጽታ መለየት የሚያስችለውን ቴክኖሎጅ  አስፈላጊው የህግ ማዕቀፍ እስከሚዘጋጅለት ድረስ ገበያ ላይ እንደማያውለው አስታወቀ፡፡

ኩባንያው በርካቶችን እያከራከረ የሚገኘውን ይህን ቴክኖሎጅ በሰዎች ላይ በደል እንዳይፈፀም የሚያስችል ፓሊሲ እስከሚዘጋጅለት ገበያ ላይ አላውለውም ሲል በትንትናው ዕለት ይፋ አድርጓል፡፡

በጣም አስፈላጊ በሆኑ የቴክኖሎጅ ውጤቶች እና የፓሊሲ ጉዳዮች ላይ በቅድሚያ መስራት እንደሚያስፈልግም ኩባንያው ገልጿል።

በዚህም መሰረት ቴክኖሎጅውን ይህን የሚያግዝ ፓሊሲ እስከሚዘጋጅ ድረስ ጥቅም ላይ እንደማያውል አስታውቋል።

የሰዎችን ማንነት በፊት መለየት የሚያስችለው መሳሪያ እንደሌሎች የቴክኖሎጅ ውጤቶች ጥንቃቄ የሚስፈልገው መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፥ ቴክኖሎጅው መርህና እሴት እንዲጠበቅ እና በሰዎች ላይ በደልና ጉዳት እንዳይደርስ የሚያደርግ ሊሆን ይገባዋልም ተብሏል፡፡

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.