የአንገት ህመምን በተፈጥሯዊ መንገድ ለማከም

የአንገት ህመም መነሻዎች በርካታ ቢሆኑም በዋናነት ጭንቀት፣ የትራስ አጠቃቀም፣ ምቹ ያልሆነ የስራ ቦታ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያለማድረግና የመሳሰሉት በመንስኤነት ይጠቀሳሉ።

አልፎ አልፎም በጉልበታቸን እና ታፋችን አካባቢ ያሉ ህመሞች ለአንገት ህመም ችግር መነሻ ሲሆኑም ይስተዋላሉ።

እስኪ የብዙዎች የጤና ችግር የሆነውን  የአንገት አካባቢ ህመምን ያለመድሃኒት ለለማከም የሚረዱ ነጥቦችን እናካፍላችሁ ።

  1. እያንዳንዱን የእጅ ጣታችንን (አስሩንም) ተራ በተራ መሳብ እና ማንቀሳቀስ በዚህ ወቅት የሚፈጠረው የጣት ማንቋቋት፤ ጥሩ ስሜት ላይፈጥርብን ይችላል ይሁንና የአንገት ህመምን ለማስታገስ የመፍትሄ እርምጃው አካል በመሆኑ ማከናወን ይኖርብናል።
  2. መዳፋችንን ወደ ውጭ እንዲታይ በማድረግ እና 10 ጣታችንን በጀርባችን አቅጣጫ ማቆላለፍ፤ እግራችንን ከፈት በማድረግ ያቆላለፍነውን እጃችንን ወደ ማጅራታችን ማሳሳብ።
  3. አሁን ደግሞ መዳፋችንን ወደ ውስጥ አይበሉባችን ፊትለፊት እየታየ ጣቶቻችንን እርስ በእርስ በማቆላለፍ እና የቀኝ እጃችንን ወደ ቀኝ የግራችንን ደግሞ ወደ ግራ ጣታችን እንደተቆላለፈ ማሳሳብ እንችላለን።
  4. አስሩንም ጣቶቻችን እንዳቆላለፍን እጃችንን በጭንቅላታችን ትይዩ ወደ ሰማይ ማሳሳብ (መዳፍ ወደ ውጪ እንዲታይ አይበሉባ በአንፃሩ ወደ ውስጥ በጭንቅላት ትይዩ መሆኑን ማረጋገጥ) ይኖርብናል።
  5. ከፍ ያለ እና እንደ ወንበር ያለ ቁሳቁስ በመጠቀም አንዱን እግራችን በወገባችን ትይዩ ቢያንስ 90 ዲግሪ እንዲሰራ በማድረግ እናሳስበው፤ ከወገብ በላይ ያለውን የሰውነት ክፍል ደግሞ ወደሚሳሳበው እግር መለጠጥ አለብን።

ዮጋ የተሰኘው እና በአብዛኛው የእስያ አገራት የተለመደው የስፖርት አይነትም የሰውነት የአንገት ህመምን ለማስቀረት  በአማራጭነት የሚተገበር መሆኑም ተጠቁሟል።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

 

Advertisement

3 Comments

Comments are closed.