ለህፃናት ጤና አስፈላጊ የሆኑ ምግቦች

ህፃናት ጤናማ ሆነው መቆየት እንዲችሉ ትኩስና ጤናማ  ምግብ እንዲያዘወትሩ ቢመከርም ህፃናቱ ለእንደዚህ አይነት ምግቦች ያላቸው ፍላጎት ዝቅተኛ መሆኑን ያመላክታሉ።

በመሆኑም ልጆች ጤናማ ሆነው እንዲያድጉ ትክክለኛውንና  አስፈላጊውን የምግብ ይዘት መመገባቸውን ቤተሰቦቻቸው ሊከታተሉ  እንደሚገባ ይነገራል፡፡

በተለይ ህጻናት በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦችን እንዳይመገቡ ማድረግና በቫይታሚን፣ ማዕድናት እና በንጥረ ነገሮች የበለፀጉ ምግቦችን እንዲያዘወትሩ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ባለሙያዎች ይገልፃሉ፡፡

ለህፃናት ጤና አፈላጊ የሆኑ ምግቦች፤

1.እንቁላል

እንቁላል በፕሮቲንና ለህጻናት የአዕምሮ እድገት የሚረዳው ዲ ኤች ኤ ንጥረ ነገር የበለጸገ በመሆኑ እጅግ አስፈላጊ ነው።

2.አሳ

በተለይ በጨዋማ ባህር የሚገኙ አሳዎች በህጻናት ተመራጭ ባይሆኑም አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን የያዙ ናቸው።

በመሆኑም ከሩዝና ሌሎች ነገሮች ጋር እየቀላቀሉ ለህፃናት ማቅረብ አስፈላጊ ነው።

3.ጥራጥሬ

የበሰለ ባቄላ፣ ጥቁር ባቄላ፣ አተር እና ሌሎች የጥራጥሬ አይነቶች እንዲመመገቡ በማድረግ ፕሮቲን እንዲያገኙ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡

4.የወተት ተዋፅኦ

የላም ወተት በፕሮቲንና ካልሺየም የበለፀገ በመሆኑ ለህጻናት በእጅጉ አስፈላጊ ነው፡፡

በመሆኑም ህፃናት ብሩህ አዕምሮ ይዘው እንዲያድጉ ከሁለት አመት እድሜያቸው ጀምሮ ሁሉንም ወተት መጠጣት ይገባቸዋል።

5.አትክልትና ፍራፍሬ

ፍራፍሬ በተፈጥሮው ጣፋጭና በህፃናት ዘንድ ተወዳጅ የሆነ ምግብ መሆኑ ይታወቃል በመሆኑም ህጻናት በየቀኑ ፍራፍሬ እንዲመገቡ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡

በተለይ ፍራፍሬዎችን በፀሀይና በሌሎች ተፈጥሯዊ መንገዶች በማድረቅ ከተለያዩ ምግቦች ጋር ለህፃናቱ ማቅረብ ይመከራል፡፡

ይህም  ህፃናቱ የተመጣጠ ምግብ እንዲያገኙ፣ ከልክ ላለፈ ውፍረት እንዳይጋለጡና የተስተካከለ የስርዓተ ምግብ መፈጨት ስነ ስርዓት እንዲኖራቸው ያስችላል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ስኳር ድንች፣ ከንፁህ ስንዴ የሚዘጋጁ ምግቦችን ከፍራፍሬ እና ከወተት ተዋጽኦ ጋር መስጠቱ፥ ለህጻናቱ አስፈላጊ መሆኑንም ባለሙያዎች ይመክራሉ።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

6 Comments

Comments are closed.