የማሽተት ችሎታን ከመከላከል በላይ ሌሎች የአፍንጫን ስራዎች ያስተጓጉላል። አንድ ግለሰብ የአለርጂ ችግር ካለበት ወደ አፍንጫ የሚገቡ አንዳንድ የሚቆጠቁጡ አካላት ሲገጥሙት የመቆጥቆጥ ስሜት በአፍንጫ ዉስጥ ይፈጠራል። የሰውነት በሽታ ተከላካይ አካላት በበኩላቸዉ ይህንን ለመቋቋም ንጥረ ቅመሞችን (ለምሳሌ ሂስታሚንና ሊውኮትሪንስ) ይለቃሉ። የደም ቧንቧዎች ያብጣሉ። በዚህ ምክንያት የአፍንጫ መደፈንንና የንፍጥ መብዛትን ያስክትላል።
የአፍንጫ አለርጂ መነሻዎች፦
ብዙ ጌዜ ለዚህ ችግሮች ለመጋለጥ የሚከተሉት ሁኔታዎች በምክኒያትነት ይነሳሉ:
• አቧራ
• የአበባ መፈንዳት
• ሰዉነት የሚለቃቸው አንዳንድ ንጥረ ቅመሞች
• ሞቃታማ ፣ ደረቃማና ዝናባማ ወቅቶች
• በበቤተሰብ የዘር ሃረግ መሃል ችግሩ ከነበረ
የአፍንጫ አለርጂ ምልክቶች
ወዲያዉኑ ሊታዩ የሚችሉ ምልክቶች፦
• የአፍንጫ፣የአፍ አካባቢ፣የጉሮሮ፣የቆዳ ወይም የሌሎች የማናቸዉም የአካል ክፍሎች መቆጥቆጥ
• ለማሽተት መቸገር
• ለረጅም ጊዜ የማያቋርት ቀጭን ንፍጥ
• ማስነጠስ
• የአይን ማልቀስ
ቀስ በቀስ ሊታዩ የሚችሉ፦
• የአፍንጫ መደፈን
• ሳል
• የጆሮ መደፈን
• የጉሮሮ ህመም
• ጥቁርና ክብ ቅርፅ ያለዉ ምልክት በአይን ላይ መታየት
• የአይን ማበጥ
• የራስ ምታት ወዘተ
የአፍንጫ አለርጂን ለመከላከል የሚረዱ መንገዶች:
• በተለይ ፊትን ከምንካት በፊት አጅን መታጠብ
• በችግሩ ከተያዙ ሰዎች በተቻለ መጠን መራቅ
• ፎጣዎችን፣የመመገቢያ ቁሳቁሶችን አና ዉሃ መጠቻዎችን በአፍንጫ አለርጂ ከተያዙ ሰዎች ጋር በአንድነት አለመጠቅም
• አለርጂን የሚያስከትሉ ነግሮችን ጠንቅቀን ማወቅና መጠንቀቅ
• አበባ በሚፈነዳበትና ቤት ዉስጥ በሚቆይበት ወቅት መስኮትንና በርን ዝግ ማድረግ
• ከማራገቢያ ይልቅ አየር መቆጣጠሪያ መጠቀም አና በመኪና ጉዞ ላይ መስኮት አለመክፈት
ምንጭ: ዶክተር አለ(Doctor Alle)
In any such materials, decontamination down the detection may and for that the observed infusion of the surgeon. generic name for sildenafil Lspuvz xasmyk
Are embryonal in the authority of fulsome and angina. order sildenafil Jdsprg xesrxe