በመመልከት መማር

ሰዎች በማየት ይማራሉ ፡፡ ማየት በጣም ሀይል ያለው መማሪያ ነው፡፡ ልጆች እቤት ውስጥ እና ከቤት ውጪ ብዙ ነገሮችን በማየት ይማራሉ፡፡ እናትና አባት ሲከባበሩ ፣ሲፋቀሩ፣ሲረዳዱ ወዘተ ልጆቻቸውን በተዘዋዋሪ መንገድ እነዚህን በሃሪያቶች ያስተምራሉ፡፡በሌላ በኩል ደሞ ሲሰዳደቡ ፣ሲጣሉ ወዘተ ለልጆቻቸው መጥፎ ነገር እያስተማሩ እነደሆነ ሊረዱ ይገባል፡፡

ልጆች መቼ በማየት ይማራሉ ፡-
– ሰዎች በሰሩት ስራ ሲሸለሙ ሲመለከቱ
– በራሳቸው ችሎታ እምነት ሲያጡ
– ከራሳቸው ጋር ተመሳሳይ እድሜና ችሎታ ያላቸው ሰዎች ሲያደረጉ ሲያዩ
– ሰዎች በሰሩት ጥፋት ሲቀጡ ሲያዩ
– ሰዎች በሰሩት ስራ በማህበረሰብ ውሥጥ አድናቆት እና ተቀባይነት ሲያገኙ
– ሰዎች አዳጋች እና አስጊ ነገሮች ውስጥ ሲሆኑ ሲያዩ ወዘተ

በማየት መማር ጥሩም መጥፎም ጎን አለው
1. ለልጆች መጥፎ ነገሮች ሲወገዙ ጥሩ የሰሩ ሰዎች ሲወደሱ በማየት ጥሩ ነገሮችን እንደሚማሩ መጥፎ ነገሮችን እንዳይፈጽሙ ማስተማር ይቻላል፡፡ለምሳሌ ሙስናን ለመዋጋት አንዱ መንገድ ሙስና የሰሩ ሰዎችን ላይ ተገቢውን ቅጣት ከመጣል በተጨማሪ ቅጣቱን ለሌላው በማሳየት ሙስናን የሚጸየፍ ማህበረሰብን መፍጠር ይቻላል፡፡
2. እቤት ውስጥ ወላጆች ባሉን ግንኙነት በመከባበር በመነጋገር በመደማመጥ ልጆቻችን እነዚህን መልካም ባህሪያቶችን እንዲማሩ ማድረግ ይቻላል፡፡
3. በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ አርአያ የሚሆኑ ሰዎችን በማቅረብ ለወጣቶች እና ለልጆች ማስተማር ይቻላል፡፡ ብዙ አርአያ መሆን የሚችሉ ሰዎች አሉ የነዚህን ሰዎች ተሞክሮ ወደ ሚዲያ በማምጣት ለልጆች እና ለወጣቶች አርአያ እንዲሆኑ ማድረግ ይቻላል፡፡
4. ልጆች በማየት አሉታዊ ነገሮችንም ሊማሩ ይችላሉ መጥፎ ስራ የሰሩ ሰዎች ሲሸለሙ ሲመለከቱ ያንን መጥፎ ስራ ይማራሉ፣ እቤት ውስጥ በምናሳየው ተገቢ ያልሆነ ባህሪ ልጆቻችን ተገቢ ያልሆነ ነገርን ሊማሩ ይችላሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ ሚዲያዎች የሚተላለፉ አንዳንድ ፕሮግራሞች ፣ድራማዎች፣ፊልሞች ለልጆች መጥፎ ነገሮችን ሊያስተምሩ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ወላጆች ልጆች በእድሜያቸው ልክ የሆኑ ነገሮችን ብቻ እንዲመለከቱ ማድረግ ይጠበቅብናል በተጨማሪም የሚሰሩ ፊልሞች እና ድራማዎች ላይ የእድሜ ገደብ ሊኖራቸው ይገባል::

ምንጭ: ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.