የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች አጠቃቀም የልጆች ጤናማ እንቅልፍ ላይ ተጽህኖ የለውም

የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች አጠቃቀም በልጆች ጤናማ እንቅልፍ ላይ ተጽህኖ እንደሌለው ተመራማሪዎች ገለጹ።

የኦክስፎርድ ዩንቨርሲቲ ተመራመሪዎቹ ለረጅም ጊዜ ከኤሌከትሮኒክስ መሳሪያዎች ስክርን ጋር ግንኙነት በላቸው ህጻነት ላይ በአደረጉት ጥናት እንዳረጋገጡት የህጻነቱ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች አጠቃቀም ህጻነቱ እንቅልፍ ላይ ተጽህኖ የሌለለው መሆኑን አረጋግጠዋል።

ጥናቱ እድሜያቸው ከ6 ወር አስከ 17 ዓመት በሆኑ 50 ሺህ212 የአሜሪካ ህጻነት ላይ የተከሄደ ሲሆን፥ መረጃው በአሜረካ ብሄራዊ ጥናት የተሰበሰበ መሆኑም ነተነግሯል።

ቢዚህ ጥናት መሰረትም ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን የማይጠቀሙ ህፃናት በአማካይ 8 ሰዓት ከ51 ደቂቃ የሚተኙ ሲሆን፥ በአንጻሩ በቀን እስከ 8 ሰዓት ያህል እሰክሪን ላይ የሚያሳልፉ ህፃናት 8 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ያህል እንደሚተኙ ተገልጿል።

ከኤለከትሮኒክስ መሳሪያዎች ስክሪን ጋር ግንኙነት የሌላቸው ህጻናት ኬሎች በጥናቱ ከተካተቱት ህፃነት በአመካይ የ30 ደቂቃ እንቅልፍ ልዩነት የታየ ሲሆን፥ ህፃናቱ ከኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት የጤናማ እንቅልፋቸው ሁኔታ ላይ ተጽህኖ የሌለው መሆኑ ተመላክቷል።

ቀደም ሲል ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የወጡ ጥናቶች ለረጀም ጊዚያት የኤሌክትሮኒከስ ስክሪኖች ላይ የሚቆዩ ህፃናት የተስተካከለ አንቅልፍ ለማግኘት እንደሚቸገሩ ማመላከታቸውን ዘገባው ያስረዳል።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.