የማህጸን ፈሳሽ ከሴት ብልት የሚወጣ ፈሳሽ ሲሆን በውስጡ የሴት ብልት ሴሌች፣ የማህጸን በር ሴሎች ፣ ባክተሪያ ፣ ልፋጭ እና ውሃ የያዘ ነው።
የማህጸን ፈሳሽ ተፈጥሯዊ (normal) ሊሆን ይችላል?
አዎ ከማህጸን የሚወጣው ፈሳሽ ተፈጥሮአዊ ሊሆን ይችላል ፡፡ተፈጥሯዊ የሚባለው ሁሉም ሴቶች በተወሰነ ደረጃ የሚያመነጩት በአብዛኛው ውሀማ መልክ ያለው እና የመጎተት ባህርይ ያለው ሲሆን ብዛቱም በሀያ አራት ሰዓት ውስጥ ከአንድ እስከ አራት ሲሲ የሚደርስ ነው፡፡ ጠረኑን በሚመለከትም በአብዛኛው ምንም ሽታ አይኖረውም ፡፡
አንዳንድ ሁኔታዎች ተፈጥሯዊ የማህጸን ፈሳሽ እንዲጨምር ሊያደርጉ ይችላሉ። እነዚህም የሚከተሉት ናቸዉ
– በእርግዝና ጊዜ ከሰውነት ተፈጥሮአዊ ቅመሞች መጨመር ጋር ተያይዞ የሚመጣ ፈሳሽ ሊኖር ይችላል።
– የእርግዝና መከላከያ ማለትም ሆርሞን ያያዙ መከላከያዎችን የሚጠቀሙ ሴቶች የፈሰሹ መጠን ሊጨምርባቸው ይችላል፡፡
– ወር አበባ ዑደት ግማሽ ላይ( የወር አበባ ከመምጣቱ ከአስራ አራት ቀን በፊት) እንቁላል አኩርታ የምትወጣበት ጊዜ የማህጸን ፈሳሽ ይጨምራል፡፡
የማህጸን ፈሳሽ ተፈጥሯዊ አይደለም(abnormal vaginal discharge) የሚባለው ምን ሲታይበት ነው?
ከላይ ከተጠቀሱት ተፈጥሮአዊ ሁኔታዎች ውጭ በሆነ መንገድ የሚከሰት የማህጸን ፈሳሽ ከተፈጥሮአዊው (ከጤነኛ) ፈሳሽነት ወደ ተፈጥሯዊ ያልሆነ ፈሳሽነት ተለውጧል ማለት ይቻላል፡፡ የፈሳሹ መልክ እንዲሁም ጠረኑ እና ብዛቱ ከተለመደው ውጭ ከሆነ ተፈጥሯዊ አይደለም ማለት ነው፡፡
በተጨማሪም ከስር የተዘረዘሩት ምልክቶች ከታዩ ፈሳሹ ተፈጥሯዊ አይደለም ማለት ይቻላል ። እነዚህም
– የብልት ማሳከክ
– የብልት መቅላት ፣ ህመም ወይም እብጠት
– አረፋማ ፈሳሽ ፣ አረንጓዴ /ቢጫ ፈሳሽ ፣ ደም የቀላቀለ ፈሳሽ
– መጥፎ ጠረን ያለው ፈሳሽ
-ሽንት ማቃጠል ፣ በወሲብ ጊዜ ህመም
– የታችኛው የሆድ ክፍል ህመም እና
– ትኩሳት ናቸዉ ።
ተፈጥሮአዊ የሆነው የማህጸን ፈሳሽ ጤነኛ አይደለም ከሚባልበት ደረጃ የሚደርሰው በምን ምክንያት ነው?
ምክንያቶቹ በርካታ ቢሆኑም ዋና ዋናዎቹ ግን የሚከተሉት ናቸዉ ፡፡
– ከጀርም ጋር የተያያዘ ወይም የማህጸን ኢንፌክሽን።በኢንፌክሽን ወይንም በጀርም አማካኝነት የሚመጣው ፈሳሽ እንደመንስኤው ሁኔታው ይለያያል፡፡ ይህ ችግር በአባላዘር በሽታ ወይንም ከአባላዘር በሽታ ጋር ባልተያያዘ መንገድ ሊከሰት ይችላል፡፡
– ባእድ ነገር ከብልት ውስጥ ሲረሳ እና የሰውነት መቆጣት ሲያስከትል። ለምሳሌ ታምፖን ወይም ኮንዶም
– በማረጥ ምክንያት የሚከሰት ።በእድሜ ወይንም በሌላ ምክንያት የወር አበባ ሲደርቅ ሴቶች የሰውነታቸው ሆርሞን ስለሚያንስ ብልታቸው ወደ መድረቅ ያደላል፡፡ አንዳንዴ ግን ወደፈሳሽ የማምራት ሁኔታዎችም ይስተዋላሉ፡፡
-ሴቶች ኬሚካልን ወይም ሽቶ ያለው ሳሙና በብልታቸው አካባቢ የሚጠቀሙ ከሆነ ኬሚካሎቹ ፈሳሽን የሚያበዙበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል ።
– ለሰውነት ተስማሚ ያልሆኑ ልብሶችን ማለትም የውስጥ ሱሪ እና ሱሪ በጣም ሰውነትን የሚያጠብቁ ወይንም ከናይለን የተሰሩ ፓንቶች ለብልት መቆጣትና ተፈጥሯዊ ላልሆነ የማህጸን ፈሳሽ መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ ።
– በማህጸን በር ላይ ወይንም የሴት ብልት ውስጥ እጢዎች ካሉም የማህጸን ፈሳሽን ይበዛል፡፡
ተፈጥሯዊ ያልሆነ የማህጸን ፈሳሽ በራስ ማከም ይቻላል?
ተፈጥሯዊ ያልሆነ የማህጸን ፈሳሽ በራስ ለማከም መሞከር ሁኔታው ሊያባብሰው ስለሚችል አይመከርም ።
ተፈጥሯዊ ላልሆነ የማህጸን ፈሳሽ መፍትሔው ምንድን ነው?
ተፈጥሯዊ ያልሆነ የማህጸን ፈሳሽ በሚታይበት ጊዜ የጤና ባለሙያ ጋ ቀርቦ መታየት ግድ ይላል። ባለሙያው አስፈላጊ የጤና መረጃ በመውሰድና ምርመራ በማድረግ መንስኤውን ለማወቅ ይጥራል። ከፈሳሹም ናሙና በመውሰድ ኢንፌክሽን መኖር አለመኖሩን ያጣራል።
ህክምናው መንስኤውን መሰረተ ያደረገ ነው ። ለምሳሌ ለተለያዩ የማህጸን ኢንፌክሽን አይነቶች የተለያዩ መድሃኒቶች ሊታዘዙ ይችላሉ ።
የፈሳሹ መንስኤ እስኪታወቅ ድረስ የግብረ ስጋ ግንኙነት ከማድረግ መቆጠብ ያስፈልጋል።የማህጸን ፈሳሹ መንስኤው የአባላዘር በሽታ ሆኖ ከተግኘ ባለቤቷም ህክምና እንዲያደርግ ይደረጋል።
ተፈጥሯዊ ያልሆነ የማህጸን ፈሳሽ እንዴት መከላከል ይቻላል?
ከስር የተዘረዘሩት ነገሮች በመተግበር ተፈጥሯዊ ያልሆነ የማህጸን ፈሳሽን በተወሰነ መልኩ መከላከል ይቻላል።
– የብልት ከንፈር ለብ ባለ ውሃ ብቻ ማጠብ
– ገላዎን ሲታጠቡ ለብ ያለ ንጹሀ ውሃ መጠቀም ፣ ሽቶ ያላቸው የግል ንጽህና መጠበቂያ ተዋጽኦዎችን አለመጠቀም
– አንዳንድ ኬሚካሎች(sprays or powders) ወደ የሴት ብልት አለማስገባት
– የሴት ብልት ውስጡን አለማጠብ(Not douching)
የሴት ብልት ውስጥ ባክቴሪያዎች አሉ፡፡ እነዚያ ባክሪያዎች የራሳቸውን ቁጥር የጠበቁ እና ተመጣጥነው ያሉ ናቸው፡፡ ከባክሪያዎቹ ውስጥ በብዛት የሚገኘው lactobacillus የሚባለው ሲሆን ይህ ባክሪያ ዋና ስራው ከማህጸን ግድግዳ ውስጥ ያለውን ግሉኮስ በመጠቀም አሲድ ማመንጨት ነው፡፡ ያ አሲድ ደግሞ የሴትን ማህጸን ወይንም ብልት ከተለያዩ ጀርሞች ይከላከላል፡፡ lactobacillus የተሰኘው ባክሪያ በመታጠብ ቁጥሩ የሚያንስ ከሆነ ግን ሌሎች የማይፈለጉት ባክሪያዎች ይበልጥ ይራቡና ወደ ፈሳሽ ይለወጣሉ፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ መጥፎ ጠረን ያለው እና ብዛት ያለው ፈሳሽ መፍሰስ ይጀምራል፡፡ በዚሁ ምክኒያት የሴት ብልት ውስጡን ማጠብ አስፈላጊ አይደለም።
– ከተጸዳዱ በኋላ ቤቢ ዋይፐር ወይም ሽቶ ያለው የመጸዳጃ ወረቀት አለመጠቀም
ከላይ የተዘረዘሩት ነገሮችን ተግባራዊ በማድረግ ተፈጥሯዊ ያልሆነ የማህጸን ፈሳሽ ይከላከሉ።
ምንጭ: ዶክተር አለ(Doctor Alle)
Nearly men stool from attrition and brachial plexus which may. buy generic sildenafil online Udohtc mvnqgu