የደም ግፊት መጠንን የሚለካው ፕላስተር

ተመራማሪዎች የደም ግፊታችንን መጠን የሚለካ አዲስ ፕላስተር መስራታቸው ተነግሯል።

አንድ ኢንች ርዝመት ያለው ፕላስተሩ በአንገታችን ላይ በመለጠፍ ወደ አእምሯችን በሚመላለሰው ደም ላይ በመመስረት አጠቃላይ የደም ግፊታችንን መጠን የሚለካ ነው።

ፕላስተሩ በአንገታችን ላይ ከተጠለፈ በኋላ ወደ የደም ቧንቧችን ድምጽ የሚለቅ ሲሆን፥ ደምጹ የሚፈጥረው ንዝረት ላይ ተመስርቶም የደም ግፊት መጠንን እንደሚለካም ተነግሯል።

ድምጹ የተጓዘበት ፍጥነትን በመለካትም የደም ስሮቻችን ስፋት በምን ደረጃ ላይ አንደሚገኙ እንደሚያሰላም ነው የተገለፀው።

ይህ የሚሆነውም በፕላስተሩ ላይ የተገጠመው ቴክኖሎጂ ያገኘውን መረጃ ወደ ኮምፒውተር በመላክ ሲሆን፥ ኮምፒውተሩም ባገኘው መረጃ ላይ በመመስረት የደም ግፊታችንን መጠን አስልቶ ያስቀምጣል።

ፕላስተሩ በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ የተሰራ መሆኑም ተነግሯል።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

3 Comments

Comments are closed.