ፓልም የሚል መጠሪያ ያለው አነስተኛ የቅንጦት የእጅ ስልክ ለገበያ ሊቀርብ ነው

ፓልም የሚል መጠሪያ ያለው አነስተኛ የቅንጦት የእጅ ስልክ ለገበያ ሊቀርብ ነው።

አነስተኛ መጠን ያለው ስማርት ስልክ ፓልም በሚል መጠሪያ በቅርቡ የአሜሪካን ገበያ ይቀላቀላል ተብሏል።

አዲሱ የቅንጦት ስማርት የእጅ ስልክ የክሬዲት ካርድ መጠን ያለው ሲሆን፥ ሁለት ካሜራዎች እንዳሉት ታውቋል።

የጆሮ ማዳመጫ ገመድ መቀበያ የሌለው ሲሆን፥ በገመድ አልባ ሲስተም ቻርጅ እንደሚደረግም ነው የተገለጸው።

ቴክኖሎጂው መደበኛ ስማርት ስልኮች የሚሰጡትን አገልግሎቶች የሚሰጥ ሲሆን፥ የራሱ የፈጠራ መብት ባለቤትነት ያለው እንደሆነም ተነግሯል።

የ349 ዶላር ዋጋ እንደሚቆረጥለት የተነገረው ይህ ቴክኖሎጂ ከፈረንጆቹ ህዳር ወር ጀምሮ የአሜሪካን ገበያ እንደሚቀላቀል ዘገባው ያስረዳል።

ለአጠቃቀም ምቹ እና በመጠኑም አነስተኛ መሆኑ ከመደበኛ የእስማረት ስልኮች በተሻለ ተፈላፈጊነቱ እንዲጨምር እንደሚያደርገውም ተጠቁሟል።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.