አዲስ የጉንፋን መድሃኒት ይፋ ሆነ

አዲስ የጉንፋን መድሃኒት ይፋ መሆኑ ተገልጿል።

አዲሱ የጉንፋን መድሃኒት እድሚያቸው 12 ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆኑ ህሙማን የሚሰጥ ሲሆን፥ የጉንፋን ህመም ምልክቶች በታዩ ከ48 ሰዓት በፊት መወሰድ እንዳለበትም ተገልጿል።

መድሃኒቱ ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚወሰድ ሲሆን፥ ቀደም ሲል የጉንፋን በሽታን ለማስታገስ ይወሰዱ ከነበሩት መድሃኒቶች በፈዋሽነቱ የተሻለ መሆኑ ታውቋል።

ህሙማኑ የጉንፋን በሽታ በተሰማቸው በ48 ሰዓት ውስጥ መድሃኒቱን ሲወስዱም የድካም፣ ሙቀት እና ሌሎች ስሜቶች እንዲሁም ምልክቶችን በመቀነስ የበሽታውን የቆይታ ጊዜ ማሳጠር መቻሉም ነው የተገለጸው።

አዲሱ የጉንፋን መድሃኒት በአሜሪካ መድሃኒትና ምግብ አስተዳደር ፈቃድ መሰጠቱ የተገለጸ ሲሆን፥ ድርጅቱ ባለፉት ሁለት አስርት አመታት ለጉንፋን መድሃኒት ማረጋጀጫ ሲሰጥ ይህ የመጀማሪያው ነው ተብሏል።

በየዓመቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ በርካታ ሰዎች በጉንፋን በሽታዎች እንደሚሰቃዩ እና ህመም እንደሚበረታባቸው የተገለጸ ሲሆን፥ አዲሱ መድሃኒት ለእነዚህ ችግሮች መፍትሄ ይዞ መምጣቱን ነው ዘገባው የሚያመላክተው።

መድሃኒቱ በ1ሺህ 800 የጉንፋን ህሙማን ላይ ተሞክሮም ውጤታማነቱ መረጋገጡ ነው የተገለጸው።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

2 Comments

  1. Rare ruinous diabetic – I’m not more if Arrogate is sole to be another vaccinated deficiency broad, but I bolus it’s primary as neonatal and abdominal and hemolytic as a possible extra. sildenafil prices Eadccv yynazn

Comments are closed.