ጭንቀት በህፃናት

የጭንቀት ስሜት ወይም ጭንቀት በዕለት ከዕለት ህይወት የሚጠበቅ ክስተት ነው፡፡ ማንኛውም ሰው ቢሆን በሆነ ጊዜ ውስጥ መጨነቁ አይቀርም :: ከአነስተኛ እስከ መካከለኛ ጭንቀት ለልጆች ጠቃሚ ነው ምክንያቱም ትኩረታቸው፣ ሀይላቸው ላይ እንዲያተኩሩ ያግዛቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ፣ በከፍተኛ ጭንቀት፣ ወይም ሁለነተናዊ የጭንቀት ህመም ውስጥ ያሉ ልጆች ጭንቀታቸውን መቆጣጠር ስለማይችሉ በፅኑ ጭንቀት ይወጠራሉ፡፡ እነርሱም አዕምሮአቸው የተያዘ ነው ወይም በስራዎቻቸው ስኬትንና በችሎታቸው ከሌሎች አድናቆትን ወይም ተቀባይነትን ለማግኘት ሲሉ ይጨነቃሉ፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን ትክክለኛ ለመሆን ይጨነቃሉ፡፡ የጭንቀት መጠኑ በጣም ከፍተኛ ከሆነ፣ ህጻናት ረዳት የለሽ፣ከመጠን ያለፈ ውዥንብርና ፍጹም ጭንቀት ሊገጥማቸው ይችላል ወይም የተፈራው ነገር ሊያጋጥማቸው ይችላል፡፡
የዕለት ከዕለት ህይወት ይዛባል ማህበራዊ ጭንቀት ህመም፤ በሰዎች ፊት ለፊት ሆነው ምን እንደሚሉ ወይም እንደሚሰሩ የዕለት ከዕለት ህይወትን እስከሚጎዳ ድረስ በጣም መጨነቅ ሊይዝ ይችላል፡፡
የፍርሀት በሽታ፤ የተወሰነ ልዩ ነገር፣ ሁኔታ ወይም ተግባር ማለትም እንደ ሸረሪት፣ ከፍታ ወይም ትንሽ ቦታዎች ያሉ ነገሮችን በጣም መፍራት ለከፍተኛ ጭንቀት ይዳርጋቸዋል፡፡

ምልክቶቹ፡-
– የከፍተኛ ፍርሀት ህመም
– ተደጋጋሚ አስፈሪ ጥቃት ወይም ድንገተኛ
– ከፍተኛ ፍርሀት ማጋጠም
– የትንፋሽ እጥረትና ፈጣን የልብ ምት
– መነጫነጭ እና ብስጩ መሆን
– መንቀጥቀጥ
– ከፍተኛ ትኩሳት እና ላብ

መፍትሄው፡-

– የልጅዎን ህመም መገንዘብ
– የልጅዎችዎን ስሜት ማድመጥ
– ልጅዎን ማበረታታት
– ማዝናናት እንዲሁም ማስተማር
– ከጭንቀት ወጣ የሚያደርጉ ተግባራት ላይ እንዲሳተፉ
– ህጻናትን በስራዎች ላይ ማሳተፍ
– ልጅዎን በንቃት ማድመጥ አጋዥና ሀይል ሰጪ ውጤት ይኖረዋል
– ልጅዎችዎ ጭንቀት ከሚፈጥሩ ነገሮች ጋር አብረው እንዳሉ በቀስታ ማሳወቅ
– የጭንቀት ምልክቶችን ለማቃለል የልጅዎን ጥረቶችን ማድነቅ የተሻለ ለውጥ ይኖረዋል፡፡

በተጨማሪም ችግሩ ከዚህ በላይ የከፋ ከሆነ ልጆን ወደ ስነ-ልቦና ሀኪም መውሰድ አስፈላጊ ነው ምክንያቱም ችግሩ ሳይስፋፋ በጊዜ መድረስ ግዴታ ስለሆነ ነው፡፡

ምንጭ: ዶክተር አለ(Doctor Alle)

 

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.