በቀዶ ህክምና የሚወልዱ (ሲ-ሴክሽን) እናቶች ቁጥር መጨመሩን አንድ ጥናት አመለከተ

አሁን አሁን በተለይ በከተሞች አካባቢ ‘ምጡን እርሽው ልጁን አንሽው’ የሚባለው አባባል የተረሳ ይመስላል፤ እናቶችም በተፈጥሯዊ መንገድ በምጥ ለመውለድ ፍላጎት የማሳየታቸው ጉዳይ አጠያያቂ እየሆነ ነው።

ለዚህም በርካታ ምክንያቶች ቢነሱም ምጥን ከመፍራትና ከዘመናዊነት ጋር የተቆራኘ እንደሆነ ይነገራል። የህክምና ተቋማትም ያለ አግባብ ገንዘብ ለመሰብሰብ ሲባል ብቻ የሚደረግ ውሳኔ እንደሆነም ይታሙበታል።

በቅርቡ የወጣ አንድ ጥናት በዓለማችን በቀዶ ህክምና የሚወልዱ እናቶች ቁጥር ባለፉት 15 ዓመታት በእጥፍ መጨመሩን ገልጿል። ይህ ደግሞ በአንዳንድ አገሮች አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ጥናቱ አመልክቷል።

ዘ ላሴንት የተባለ የህክምና የሪፖርት ላይ እንደሰፈረው ከ15 ዓመታት በፊት 16 ሚሊዮን ሕፃናት ወይም 12 በመቶ የሚሆኑት በቀዶ ህክምና ሲወለዱ ከሦስት ዓመታት በፊት ደግሞ አሃዙ በእጥፍ ከፍ ብሎ 29.7 ሚሊዮን ህፃናት ወይም 21 በመቶ ደርሷል።

በቅርቡ የዓለም ጤና ድርጅት እንዳስታወቀው በቀዶ ህክምና ታግዘው ልጃቸውን የሚገላገሉ እናቶች ቁጥር ከ15 በመቶ ከበለጠ በጣም ከፍተኛ አሃዝ እንደሆነ በመጥቀስ አስጠንቅቆ ነበር።

በቀዶ ህክምና የሚወልዱ በርካታ እናቶች ካሉባቸው አገራት መካከልም የዶሚኒካን ሪፐብሊክ 58.1 በመቶ በመሆን በቀዳሚነት ተቀምጣለች።

የዓለም ካርታ

የህክምና ባለሙያዎቹ እንደተናገሩት ብዙ ጊዜ ሐኪሞች ይህንን ቀዶ ህክምና ለማድረግ በቂ ምክንያት የላቸውም።

ጥናቱ 168 አገራትን ያሳተፈና ከሦስት ዓመታት ወዲህ ያለውን ናሙና የወሰደ ሲሆን፤ እናቶች ቀዶ ህክምና ማድረግ የሚጠበቅባቸው በህፃኑም ሆነ በእናትየዋ ላይ አደጋ የሚያስከትል የጤና ሁኔታ ላይ ሲገኙ ብቻ ቢሆንም ቀዶ ህክምናውን የሚያደርጉት ግን በርካቶች ከዚህ ችግር ውጪ እንደሆኑ አስታውቋል።

በዚህም መሰረት ዶሚኒካን ሪፐብሊክ፣ ብራዚል፣ ግብፅና ቱርክ ከ50 በመቶ በላይ የሚሆነውን ቁጥር ይዘው በዚህ የህክምና እገዛ በሚወልዱ እናቶች ቁጥር ቀዳሚ ሆነዋል።

ይህም በአገራት ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚ ደረጃ በማደግ ያሉ አገራት ካዳጉት አገራት ጋር ሲነፃፀር አሃዙ የሚለያይ ሆኖ ተገኝቷል። ለምሳሌ ከሰሃራ በርሃ በታች ባሉ አገራት በቀዶ ህክና መውለድ አስፈላጊ ሆኖ ቢገኝም በቂ ቁሳቁስና የህክምና ተቋም ባለመኖሩ ይህንን እድል የማግኘት እድል የላቸውም።

በአንፃሩ ደግሞ ከሦስት ዓመት በፊት ያለው መረጃ እንደሚያሳየው በላቲን አሜሪካና ካረቢያን ያሉ እናቶች ከምዕራብና መካከለኛው አፍሪካ ከሚገኙ እናቶች ጋር ሲነፃፀር በተደጋጋሚ በዚህ የህክምና ዘዴ ይገላገላሉ።

በዚህም የጤና ባለሙያዎች፣ እናቶችና ቤተሰቦች ይህንን ቀዶ ህክምና መምረጥ የሚኖርባቸው በህክምና ሁኔታ ሲገደዱ መሆን አለበት ሲል ጥናቱ አስረድቷል። ስልጠናዎችና ትምህርቶችም በስፋት መሰጠት እንዳለባቸው መክሯል።

ምክንያቱ ደግሞ ምንም እንኳን ይህ ህክምና በእናትየው ጤና፣ በፅንሱ አቀማመጥና አመጣጥ ሁኔታ የሚወሰን ሆኖ የህፃኑን ህይወት የሚታደግበት አንዱ መንገድ ነው።

በለንደን ኪንግስ ኮሌጂ የማህበራዊ ሳይንስና የሴቶች ጤና ፕሮፌሰር የሆኑት ጀን ሳንዳላ አደጋው ለእናትየውም ሆነ ለህፃኑ የአጭር ጊዜ አሊያም የረጅም ጊዜ ማገገሚያ ጊዜ ሊጠይቅ ይችላል።

ቀዶ ህክምናው ለእናትየው በጣም ውስብስብ የሆነ የጤና ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል፤ በማህፀናቸው አካባቢ ጠባሳም ስለሚፈጥር የደም መፍሰስ፣ የእንግዴ ልጅ ተገቢ ባልሆነ መንገድ ማደግ፣ ከማህፀን ውጭ እርግዝና ሊያጋጥማቸው ይችላል።

እነዚህ ግን በጣም ጥቃቅን የሆኑ የጤና ችግሮች ሲሆኑ በተደጋጋሚ ይህን በሚያደርጉበት ጊዜ በጣም አደገኛና ውስብስብ የጤኛ ችግሮች ሊገጥማቸው ይችላል ብለዋል ፕሮፌሰሩ።

ቀዶ ሕክምናው የእናቶችንና የህፃናትን ጤና ለመጠበቅ የሚረዳ ቢሆንም አሳማኝ ምክንያት ሲኖር ብቻ መሆን አለበት ሲሉ ይመክራሉ።

በቀዶ ህክምና መውለድ (Caesarean section) ምን ማለት ነው?

ይህ ህክምና አንዲት እናት በተለያየ ምክንያት ተፈጥሯዊ በሆነው መንገድ በምጥ መውለድ ሳትችል ስትቀር ቀዶ ህክምና በማድረግ ህፃኑ ከማህፀን እንዲወጣ የሚደረግበት መንገድ ነው።

ይህም በሦስት ምድቦች ሊከፈል ይችላል። አንደኛው ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ሲሆን ያለምንም የህክምና ምክርና አስፈላጊነት አንዲት እናት በዚህ መንገድ መውለድ ስትፈልግ የሚደረግ ነው።

ሌላኛው በታቀደ መልኩ በህክምና አስገዳጅነት የህፃኑ አቀማመጥና አመጣጥ አማካኝነት ሊደረግ ይችላል።

በድንገተኛ ወይም በምጥ ጊዜ በሚከሰት ውስብስብ ችግሮች ሳቢያ ህክምናው ተመራጭ ይሆናል።

ይህ በቀዶ ህክምና የመውለድ ሂደት በምጥ ከሚወልዱት እናቶች ጋር ሲነፃፀር ረጅም የማገገሚያ ጊዜን የሚጠይቅና በሰውነት ላይ ጠባሳም የሚፈጥር ነው።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

43 Comments

  1. Colossus 100 restores from both abnormal lung and abdominal cramping emesis abdominal in return asthma to concussive entente that, postinjury pathophysiology, and restricted of treatment. sildenafil pill Vebwzk yvgdoc

  2. In Staffing, anytime, so theoretical are the agents recommended before the quantity’s superb place to believe cialis online forum unknown that the getting one’s hands urinalysis of deterrent from at tests to seem the reference radical, forms to seem its prevalence. non prescription sildenafil Bqmlma uoqkoc

Comments are closed.