የበራችንን እጀታ ስነካ ለምን ይነዝረኛል?

አብዛኛውን የምንጫማቸው ጫማዎች ኤሌክትሪክን የማያስተላልፉ የፕላስቲክ ሶል አላቸው፤ በቤትም ሆነ በሌላ አካባቢዎች ስንራመድ የሚኖረው ሰበቃ በጫማችን ሶል ላይ የእስታቲካ ኤሌትሪክ ሙሌት እንዲከማች ያደርጋል፤ በጫማችን ሶል ላይ የሚፈጠረው የእስታቲካ ኤሌትሪክ ሙሌት ወደ ሰውነታችን ስርፀት እንዲኖር ያደርጋል፤በመሆኑም በዚህ ሁኔታ ላይ እያለን ኤሌክትሪክ አስተላላፊ ቁስ በምንነካበት ወቅት ይህ የተከማቸ የእስታቲካ ኤሌትሪክ ሙሌት በአንድ ጊዜ ወደ አስተላላፊው አካል ይሰደዳል፤ በዚህ ጊዜ ከፍተኛ የሆነ ንዝረት ይሰማናል፡፡

-ይህን ሁኔታ በቤት ውስጥ በጫማ በመንቀሳቀስና በባዶ እግር በመንቀሳቀስ የራሳችንን ሙከራ በማድረግ ማየትና ማረጋገጥ እንችላለን፤ በባዶ እግራችን ከተንቀሳቀስን የእስታቲካ ኤሌትሪክ ስለማይከማች እቃዎችን ስንነካ ንዝረት አይኖርም፡፡

የእስታቲካ ኤሌትሪክ ንዝረት ለጤና አሳሳቢ የሚሆንበት ሁኔታ አለ ወይ?

አብዛኛውን ጊዜ ክውታና ምቾት ከመንሳት ውጪ የከፋ ሁኔታ አያጋጥምም፤ ምናልባት እንደ ችግር ሊታይ የሚችለው ሁኔታው ሲያጋጥመን በደመነፍስ የምንወራጨው ነገር ከሌሎች ነገሮች ጋር ሊያጋጨንና ልንጎዳ እንችላለን፤ ከዚህ በተለየ ሁኔታ ግን በነዳጅ ማደያዎች አካባቢ፣ ለምሳሌ ነዳጅ ስንቀዳ ከብረት ጋር በሚኖር ንክኪ ሁኔታው ቢፈጠር እሳት የመፈጠር አጋጣሚ ሊከሰት ይችላል፡፡

የእስታቲካ ኤሌትሪክ ገጠመኝን መከላከል ይቻላል?
ይህንን ገጠመኝ ለማስቀረት ምናልባት ብዙ ሙከራዎችን በማድረግ አብዛኞቹን ማስቀረት ወይም በሌላ ዘዴ በቁጥጥር ስር ማዋል ይቻላል፤ ለምሳሌ በሮችን ስንከፍት ቀድመን በሩን በቁልፍ መንካት፣ በበሮች ላይ የሚያጋጥመንን ንዝረት ሊያስቀር ይችላል፡
ምንጭ ፡- ሰርቫይቫል

 

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.