በእርግዝና ጊዜ የሚደረጉ የጤና እንክብካቤዎች

አመጋገብን ማስተካከል
አንዲት ነፍሰጡር ሴት በየቀኑ ፍራፍሬና አትክልት (በተለይ አረንጓዴ፣ብርቱካናማና ቀይ ቀለም ያላቸውን)፣ጥራጥሬዎችን (እንደ ባቄላ፣አኩሪአተር፣ ሽንብራ ያሉትን)፣የእህል ዘሮችን (ስንዴ፣በቆሎ፣አጃንና ገብስን )፣ከእንስሳት የሚገኙ ምግቦችን (ዓሣ፣ዶሮ፣የበሬሥጋ፣እንቁላል፤ አይብ፤ ወተት እና የወተት ተዋጽኦ ) መመገብ ይገባታል።ቅባት ስኳርና ጨው በመጠኑ ብቻ ቢወሰድ ይመረጣል። ብዙ ውኃ መጠጣት አስፈላጊ ነው።እንደ ቡናና ሻይ ያሉትን ካፌይን ያላቸው መጠጦችንም ሆነ ሰውሠራሽ ማጣፈጫዎችና ቅመሞች የተጨመሩባቸውን ምግቦች ማስወገድ ጥሩ ይሆናል።
ክብደትን መቆጣጠር
አንዲት ነፍሰጡር እናት እርግዝና ከጀመረችበት ቀን አንስቶ እስከ 3ኛው ወር ድረስ 2ኪ.ግትጨምራለች፣ ከ3ኛው– 6ኛውወር 5ኪ.ግ እና ከ6ኛው– 9ኛው ወር ደግሞ ሌላ 5ኪ.ግትጨምራለች።
-አንዲት ነፍሰጡር ሴት በአጠቃላይ ከ9 -12 ኪ.ግ ትጨምራለች ማለት ነው።
ሲጋራ እና መጠጥን ማስወገድ
አንዲት ነፍሰጡር የአልኮል መጠጥ የምትጠጣና ትንባሆን ጨምሮ ሱስ የሚያስይዝ ዕፅ የምትወስድ ከሆነ የምትወልደው ልጅ አእምሮ ዘገምተኛ የአካል ጉዳተኛ ወይም የባሕርይ መዛባት ያለበት የመሆን ዕድሉ ከፍተኛ ይሆናል።የዕፅ ሱሰኛ ከሆኑ እናቶች የሚወለዱ ሕፃናት የሱሰኝነት ምልክቶች ይታይባቸዋል፡፡ከዚህም አልፎ ተርፎ ጽንሱን እስከ ማጨናገፍ የሚያደርስ ጉዳት ሊያደርሱ ስለሚያስችሉ በእርግዝና ወቅት ፈጽሞ ሊወገዱ ይገባል።
እርግዝና እና ወሲብ
ወሲባዊ ግንኙነት በእርግዝና ወራትም የሚቀጥል ተፈጥሯዊ ጉዳይ ነው፡፡ ወሲባዊ ግንኙነት ማድረግ በመጨረሻዎቹ የእርግዝና ወራት እንዲያስወግዱ ይመከራል፡፡
• በእርግዝና ወቅት ወሲባዊ ግንኙነትን እንድናስወግድ የሚያስገድዱ ምክንያቶች
– የመራቢያ አካል ላይ የሚከሰት የመድማት ወይም ቁርጠት ችግር ካለብሽ
– መንታ አልያም ከሁለት በላይ ልጆችን እንደምትወልጂ ተነግሮሽ በዛ መሰረት የመውለጃ ጊዜሽን እየጠበቅሽ ከሆነ
– ከ37 ሳምንታት በፊት የመውለድ ወይም ውርጃ ታሪክ ካለሽ
– የማህፀንሽ በር ያለጊዜ የመለጠጥ እና የመከፈት ምልክት የሚያሳይ ከሆነ
እርግዝናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
የህክምና ባለሙያዎ ካልከለከለዎ በስተቀር በእርግዝናዎ ጊዜ በብዛት ከሚመረጡ የአካልብቃት እንቅስቃሴዎች ዉስጥ አንዱ ወክ ማድረግ ነዉ (በተለይ ለጀማሪዎች)፡፡እንቅስቃሴ ከማድረግዎ በፊት ማሟሟቅና ካደረጉ በኃላ ማቀዝቀዝዎን አይዘንጉ፡፡እንቅስቃሴ በሚያደርጉበት ወቅትምይሁን በኃላ በቂ ፈሳሽ ይዉሰዱ፡፡ከመጠን በላይ ሙቀት እንዲሰማዎ አያድርጉ፡፡
በቂ እረፍት እና እንቅልፍ ያግኙ
ነፍሰጡር አናቶች በቀን የ2 ሰአትና በምሽት ደግሞ የ8 ሰአት እንቅልፍ እና እረፍት ማግኘት አለባቸው።
አለባበስዎን ያስተካክሉ
ዘና ያሉ ልብሶችና ታኮአቸው ዝቅ ያሉ ጫማዎችን በመጫማት የጀርባ ህመምን እና የልጆን ጤና ይጠብቁ።
ተከታታይ የእርግዝና ክትትል ያድርጉ
በአካባቢዎ በሚገኝ የጤና ተቋም የእርግዝና ክትትል በማድረግ በእርግዝና ወቅት የሚከሰቱ የተለያዩ ችግሮችንና በሽታዎችን ይከላከሉ።
ያልተለመዱ ምልክቶች ሲታዩ በኣስቸኳይ ሃኪሞን ያማክሩ
ለምሳሌ፡- ከብልት ዉስጥ የሚወጣ ፈሳሽ ወይም ደም ካለ፣የሆድ ህመም፣ለረዥም ሰአት የሚቆይ ራስ ምታት፣ብዥታ፣ለረዥም ግዜ የቆየ ማስመለስ፣የእግርና የፊት እብጠት ወ.ዘ.ተ… ሲታዩ በኣስቸኳይ ሃኪሞን ያማክሩ።
መድኃኒቶች
ስለ እርግዝናው የሚያውቅ ሐኪም ጉዳቱንና ጥቅሙን በጥንቃቄ አመዛዝኖ ያዘዘው ካልሆነ በስተቀር ማንኛውንም መድኃኒት መውሰድ ተገቢ አይደለም።
ለምሳሌ:- ቪታሚን ኤ ከበዛ በጽንሱ ላይ የአካል ጉዳት ሊያደርስ ይችላል።

ለኤክስሬይ ጨረር ወይም መርዛማ ለሆኑ ኬሚካሎች እንዳይጋለጡ መጠንቀቅ ይገባል

ምንጭ: ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement

7 Comments

Comments are closed.