የጮቄ ተራራዎች በምስራቅ ጐጃምና ምዕራብ ጐጃም ዞኖች በ9 ወረዳዎች ክልል ውሰጥ የሚገኝ ሲሆን ጠቅላላ ስፋቱም ወደ 53558 ሄ/ር እንደሚደርስ በአካባቢው የተደረጉ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ አካባቢው /የጮቄ አካባቢ/ በደቡብ ምዕራብ አማራ የልማት ቀጠና ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በጐጃም አካባቢ ከፍተኛው ተራራ የሚገኘው ከዚሁ ተፋሰስ ውስጥ ነው፡፡ ጮቄ ከደብረ ማርቆስ ከተማ በስተሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ 38 ኪ.ሜ ላይ ይገኛል፡፡ የጮቄን አካባቢ ከደብረ ማርቆስ ድጐ-ጽዮን ሞጣ የሚሄደው አንደኛ ደረጃ የጠጠር መኪና መንገድ እንዲሁም ከድጐ-ጽዮን ፈረስ ቤት፣ ከደ/ማርቆስ ቁይ፣ ቢቸና የሚያገናኙ አውራ መንገዶች የሚያቋርጡት በመሆኑ ጮቄን ለመጐብኘት የመንገድ ችግር አይሆንም በተለይም ከደ/ማርቆስ ድጐ-ጽዮን ያለው አውራ መንገድ የአካባቢውን ከፍተኛ ቦታዎች አቋርጦ ስለሚሄድ ቦታውን ለመጐብኘት እንደ አንድ እድል ሊወሰድ ይችላል፡፡ አካባቢው በግምት በ1ዐዐ42.ዐዐ ሰሜን ላቲቲዩድና በ372ዐ52.ዐዐ ምስራቅ ሎንግቲውድ ላይ የሚገኝ ሲሆን ከባህር ወለል በላይ ያለው ከፍታም ከ32ዐዐ እስከ 4100 ሜትር እንደሚደርስ ይገመታል፡፡ ዓመታዊ የዝናብ መጠኑ ከ9ዐዐ እስከ 14ዐዐ ሚ/ሜ እንዲሁም ዓመታዋ የሙቀት መጠኑ ከዐ⁰с እስከ 2ዐ⁰с ይደርሳል፡፡ የጮቄ ተፋሰስ 9.5 የሚሆነውን የአባይ ወንዝ የውሀ መጠን ይሸፍናል፡፡ እንዲሁም የ23 ታላላቅ ወንዞች መነሻና የ273 ታናናሽ ምንጮች መፍለቂያ ነው፡፡ የጮቄ አካባቢ በስተምስራቅ ከእነማይና እናርጂ እናውጋ ወረዳዎች፣ በስተሰሜን ምስራቅ ከሁለት እጁ እነሴ፣ በስተሰሜን ከቢቡኝ፣ በምዕራብ ከማቻከል፣ በስተደቡብ ከስናን እንዲሁም በስተደቡብ ምስራቅ ከደባይ ጥላት ግን ወረዳዎች ይዋሰናል፡፡
የመሬት አቀማመጥ
የጮቄ አካባቢ የመሬት አቀማመጥ 86 ከመቶ ተራራማ፣ 1.5 ከመቶ ሸለቆማና 12.5 ከመቶ ሜዳማ እንደሆነና ከአካባቢው የተደረጉ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡
የስርዓተ-ምህዳር ሁኔታ፤
የጮቆ አካባቢ የAfrotropical Hihland biome እና የአፍሮ አልፓይንና ሳብ አፍሮ አልፓይን ስርዓተ-ምህዳርን የሚወክል ሲሆን በተፋሰሱ አናት ላይ የሚገኙ ጅባራ፣ ግምይ እና አሸንግድዬ የመሳሰሉት ዕፅዋት የሚገኙበት እንዲሁም የአስታውን ቀለበት ተከትሎ በዋናነት የአስታ ሽፋን አለው፡፡ በተጨማሪም የአቢያንና ሌሎች ወንዞችን ተከትሎ ደኖች /Rivrine Forest/ የሚገኙበት አካባቢ ሲሆን Afrotropical Hihland biome መጠለያቸው አድርገው የተቀመጡ 16 የአዕዋፍ ዝርያዎችን እና የተለያዩ የአይጥ እና የፍልፈል ዝርያዎችንም አቅፎ የያዘ አካባቢ ነው፡፡
የዱር እንስሳት፤
የጮቄ አካባቢ ከአሁን በፊት ብዙ ታላላቅ አጥቢ የዱር እንስሳት ተጠልለው እንደቆዩበትና የቀይ ቀበሮ ታሪካዊ የመኖሪያ አካባቢ እንደነበረ የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ ሆኖም ግን አካባቢው እየደረሰበት ባለው አሉታዊ ተፅዕኖ ምክንያት የዱር እንስሳት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ በመምጣቱ የዱር እንስሳትን በቀላሉ ማየት አዳጋች ነው፡፡
ይሁን እንጅ በዚህ ጥናት በታሳቢ የማህበረሰብ ጥብቅ ስፍራው ከ16 በላይ አጥቢ የዱር እንስሳት እና ከ41 በላይ አዕዋፍት ዝርያዎች እንዳሉ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ከነዚህም ውስጥ በአሁኑ ሰዓት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚታወቁት ከአጥቢያ እንስሳት መካከል፡-
ነብር /Leopard/
ተራ ቀበሮ /Common /Golden Jackal/
ተራ ድኩላ /Common Bushbuck/
ጉሬዛ /Abyssinian colobus/
ሚዳቋ /Common Duiker/
ተራ ጅብ /Epotted Hyena/
ተራ ዝንጀሮ /Anubis Baboon/
የዱር አሳማ /Bushpij/ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
ከአዕዋፍት መካከል በዓለም አቀፍ ደረጃ በአፍሮ ትሮፒካል ሀይላንድ ባዬም /Afrotropical Hihland biome/ ክልል ውስጥ ከሚገኙ የአዕዋፍት ዝርያዎች ውስጥ 46 ያህሉ በአገራችን እንደሚገኙና ከነዚህ ውስጥ 16 የአዕዋፍት ዝርያዎች በአካባቢው ተጠልለው እንደሚኖሩ ተረጋግጧል፡፡
– Abyssinian Lyngciaw – Ethiopian Siskin
– Bagl afecht Weaver – Moorland Chet
– Brown-rumped sedeater – Nyanza Swift
– Desky Turtle-cove – Slender-Billed Starling
– Erckel’s Francilin – Spot-Breasted lapwing
– Streaky Seedeater – Thick-Billed raven
– Sweinson’s Sparrow – Wattled Ibis
– Tacazze Sunbird – White-collared pigeon
የዕፅዋት ሽፋንና አይነት፤
የጮቄ አካባቢ ከ85 በላይ የሚሆኑ የዕፅዋት ዝርያዎችን የያዘ የተፈጥሮ አካባቢ ነው፡፡ ይሀ አካባቢ በዋናነት የአፍሮ አልፓይን ስርዓተ-ምህዳር ዕፅዋትን አቅፎ የያዘ ሲሆን እንደ አስታ፣ ጅባራ፣ ግምይ፣ ኮሶ፣ ቀጋና ሌሎችም ዕፅዋት የሚገኙበት አካባቢ ሲሆን በተለይም በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ፡-
– Acanthus sennii
– Echinops Ellendekii
– Eryhrina brucei
– Euryops pinifolius
– Kniphofia foliosa
– Lobelia rhynchopetalum
አቅፎ የያዘ ሲሆን ይህንን አካባቢ የሚጠበቅበትን ሁኔታ ማመቻቸት ለጥፋት ተጋላጭ የሆነውን የአፍሮ አይፓይን ስርዓተ-ምህዳር ማልማትና መንከባከብ ነው፡፡
የቱሪዝም አቅም፤
ጮቄ በክልሉ የጥብቅ ቦታዎች አስተዳደር ስርዓት ስር አልምቶ በቱሪዝም ኢንዱስትሪው ውስጥ ለመጠቀም የሚያስችሉ አቅሞችን መለየት በዚህም የመጀመሪያ ደረጃ ጥናት ትኩረት የተሰጠው ስራ ነው፡፡ ለዚህ ስኬት የጮቄ ተፈጥሯዊ ቦታ በሀገር ውስጥና አለማቀፍ የቱሪዝም ገበያ ውስጥ ተፎካክሮ ጐብኝዎችን ለመሳብ ምን አይነት ልዩ መስህብአዊ ሀብቶችን አሰባስቧል ? ለክልሉ የቱሪዝም ልማት ያለው ድርሻ ምን ሊሆን ይችላል ? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የሚያግዙ ጠቋሚ መረጃዎች ቀጥለው ቀርበዋል፡፡
ለቱሪዝም ገበያ የመቅረብ አቅሙ፤
አንድን ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ቅርስ በቱሪዝም ኢንዱስትሪው ውስጥ ለመጠቀም ዋነኛው መሰረት፣ በውስጡ አሰባስቦ የያዛቸው ድንቃ ድንቅ መስህባዊ ሀብቶች ናቸው፡፡ ለዚህ ደግሞ፣ ቶማስና ሚድልተን /2ዐዐ3/ በአለም አቀፍ ደረጃ ልዩና ድንቅ የሚባሉ የተፈጥሮ እሴት /Exceptional Value/ መለያዎች በዝርዝር አስቀምጠዋል፡፡ በዚህ መዘርዘር የጮቄ ተራራዎች፣ በሰዎች ተፅዕኖ የብዝሀ ይህወት ሀብትና ተፈጥሯዊ ገፅታቸው የተጐዱ ቢሆንም ለቱሪዝም ገበያ ለመቅረብ የሚያበቃ ውስን አቅም እንዳላቸው ያሳያል፡፡
ከነዚህ አቅሞቹ መካከል የአካባቢው መሬት አቀማመጥና ማራኪ ውበት አንዱ ነው፡፡ ስለዚህ የጮቄ ተራሮች ተፈጥሯዊ ገፅታን መልሶ ለማልማት፣ በመጠበቅ እና ለውበቱ አድናቂና ጐብኝዎች በማስተዋወቅ፣ አካባቢው ከቱሪዝም ገበያ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ ያስችላል፡፡ በተፈጥሮ ቦታው የአዕዋፍ መመልከቻ፣ የተራራና ጉብኝታዊ ጉዞ /Hiking & Trekking/ አገልግሎቶችን ለተጠቃሚዎች ለማቅረብ ያመቻል፡፡
ከዚህ ጐን ለጐን፣ የጮቄ ተራሮች እጅግ በርካታ ከሆኑ ምንጮች ውኃ የሚያፈልቁበት ልዩ የተፈጥሮ ቦታ ነው፡፡ የአባይ ወንዝ በኢትዮጵያ ድንበር ላይ ለሚኖረው ውሀ፣ የጮቄ ተፋሰስ ከ1ዐ በመቶ ያላነሰ ድርሻውን አመንጭቶ ያቀርባል፡፡
በአባይ በገባር ወንዞች ዙሪያ ያለውን ተፈጥሯዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁነቶችን ማወቅ የሚያጓጉ የተፈጥሮ አድናቂና ጐብኝዎችን፤
በአባይ ገባር ወንዞች ላይ ሳይንሳዊ ጥናትና ምርምሮች ማድረግ የሚፈልጉ ምሁራንን፤
ለመማር ማስተማር ሂደት ደጋፊ የሆኑ መግለጫና ማስረጃዎችን ማግኘት የሚፈልጉ ዩኒቨርስቲዎችና ሌሎች የትምህርት ተቋማትን፤
ከሀገር ውሰጥና ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ወደ አካባቢው በመሳብ ለመጠቀም ያስችላል፡፡
ለክልሉ የቱሪዝም እድገትና ልማት የሚኖረው አስተዋፅኦ፤
የጮቄ ከፍተኛ ቦታዎች በአካባቢው ማህበረሰብ ተጠብቆና ለምቶ ለቱሪዝም ገበያ ቢቀርብ፣ በዙሪያው ከሚገኙ ሌሎች መስህባዊ ሀብቶች ጋር ተሳስሮ፣ ለአካባቢው የቱሪዝም እድገት ግብዓት የሚሆን ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡ ለዚህም በጮቄ ተራሮች ዙሪያና የጉዞ መስመር ውስጥ የአገራችንን ቀደምት የባህል፣ የስልጣኔና ታሪካዊ ሁነቶች ገላጭ የሆኑ በርካታ ቅርሶች ይገኛሉ፡፡
ከነዚህም መካከል በጮቄ ተራራና በአካባቢው የሚገኙ ዋና ዋና ተፈጥሯዊ፣ ባህላዊና ታሪካዊ የቱሪስት መስህብ ሀብቶችን በመለየት ለቱሪዝም ዕድገት ያላቸውን አስተዋፅኦ ግምት ውስጥ በማስገባት እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡
የጮቄና አራት መከራከር ተራራዎች፤
ይህ አካባቢ የአራት ወረዳዎች የጋራ ሀብት ሲሆን በጣም የሚያምርና አእምሮን የሚማርክ አካባቢ ነው፡፡ የጮቄ አካባቢ በምስራቅ ጐጃም ከሚገኙ ተራራዎች ሁሉ በከፍታው አንደኛ ሲሆን ከፍታውም ከባህር ወለል በላይ 4ዐ88 ሜትር ይደርሳል፡፡ የጮቄ ተራራ ሰንሰሎች በዋናነት የሰብ አፍሮ አልፓይን እና አፍሮ አልፓይን ስርዓተ-ምህዳሮች (Afro alpine Sub afroalpine Ecosysteme) ይዘው የሚገኙ ሲሆን በአካባቢው ከሚገኙ ዋና ዋና እፅዋቶች መካከል ጅባራ፣ ግምይ፣ ጓሳ፣ አስታ፣ ቅርቀሃ፣ ጥቂቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ስርዓተ-ምህዳሮች ዋነኞቹ የአባይ ወንዝ የውሃ ምንጭ ሲሆኑ የአባይ ተፋሰስ የውሃ ማማ እንዲሆኑ ይታመናል፡፡
በአጠቃላይ የአባይ ገባር የሆኑ የ23 ትላልቅና የ273 ትናንሽ ወንዞች መፍለቂያ ናቸው፡፡ ከዚህ ሌላ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳትና የተፈጥሮ ታሪክ ማህበር (Ethiopian Wildlife and Natural History Society) በዓለም አቀፍ ደረጃ በአፍሮ ትሮፒካል ሃይላንድ ባዮም (Life International) (Afrotropical Highland Biome) ክልል ውስጥ ከሚገኙ የአዕዋፍት ዝርያዎች ውስጥ 49 ያህሉ በሀገራችን እንደሚገኙና ከእነዚህ ውስጥ 16 የአዕዋፍት ዝርያዎች በተራራው ውስጥ በአካባቢው ተጠልለው እንዲኖሩ አስቀምጠናል፡፡ ከዚህ ሌላ በሀገራችን ከሚገኙ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመጥፋት የተቃረቡ (Globally threatened) 31 ዝርያዎች ውስጥ አንዱ Abyssinian Longelaw (Macronyx Flavicollis) ይገኝበታል፡፡በአካባቢው 1995 እ.ኤ.አ በተደረገ ዳሰሳ ጥናት 49 ያህል የአዕዋፋት ዝርያዎች እንደሚገኙ ያመለክታል፡፡
በውስጡ የሚገኙ ብርቅዬ እና ድንቅዬ ዝርያዎች /Endemicity/፤
ከአዕዋፍት ዝርያዎች፡-
– Abyssinian longclaw
ከእፅዋት ዝርያዎች ውስጥ፡-
– Acanthus sennii
– Echinops ellenbeckii
– Erythrina brucei
– Euryops pinifolius
– Kniphofia foliosa
– Lobelia rhynchopetalum ይገኙበታል፡፡
Comments are closed.
Are tables that stimulate to serious liver. herbal sildenafil Yikamp yzpynj